ተማምኜ (Temamegnie) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

ላመስግን ፡ የኔጌታ ፡ ላመስግን
ላመስግን ፡ ደጋግሜ ፡ ላመስግን
በጠላቴ ፡ ሰፍር ፡ እሮሮ ፡ ሲሰማ
ለእኔ ፡ ግን ፡ በዛልኝ ፡ የምሥጋና ፡ ዜማ

ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ትልቁ ፡ ተራራ
ደልዳላ ፡ ሆነልኝ ፡ ስምህን ፡ ስጠራ
ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ትልቁ ፡ ተራራ
ደልዳላ ፡ ሆነልኝ ፡ ስምህን ፡ ስጠራ

አዝተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x)
በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ

አልጥልህም ፡ ብለህ ፡ በፍቅርህ ፡ ጠርተኽኝ ፡ ፀጋን ፡ አለበስከኝ
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ተከናወነልኝ ፡ ሞገስ ፡ ሆነህልኝ
እንድም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ከኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው
ሁሉም ፡ ያማረልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ ነው

አዝተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x)
በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ

ውድቀቴን ፡ በሚሻው ፡ በጠላቴ ፡ ላይ (፪x)
ከፍ ፡ ከፍ ፡ አረከኝ ፡ ክብርህ ፡ እንዲታይ (፪x)
ልቤ ፡ በማዳንህ ፡ እየተደነቀ (፪x)
ለታላቅነትህ ፡ ዜማን ፡ አፈለቀ (፪x)

አዝተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ተማምኜ (፪x)
በዘላለሙ ፡ ክንድህ ፡ በቅፍህ ፡ ታምኜ