ትልቅ (Teleq) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

የዘለዓለም ፡ መኖሪያዬ
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ማረፊያዬ
ታምኘብህ ፡ አላፈርኩም
በምድረበዳ ፡ አልቀረሁም

አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x)
ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ

በክንዶችህ ፡ አየተደገፍኩ
አቤት ፡ ባንተ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩ
ማዳንህን ፡ አይቻለሁ
ስለውለታህ ፡ እዝምራለሁ

አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x)
ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጠቢባኖች
የምድር ፡ ላይ ፡ ኃያላኖች
ሁሉም ፡ ወድቀው ፡ ተረስተዋል
አንተ ፡ ብቻ ፡ ያው ፡ ነህ ፡ ተከብረሃል

አዝ፦ ትልቅ ፡ ያየሁት ፡ አንተን ፡ ብቻ
በምድር ፡ በሰማይ ፡ የለህ ፡ አቻ
እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ
ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ትለያለህ (፪x)
ካየሁት ፡ ሁሉ ፡ ትበልጣለህ