ቃል ፡ ተናገር (Qal Tenager) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አዝ፦ አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ቃል ፡ ተናገር ፡ እንጂ ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጊዜ ፡ የማይሽረው ፡ ባለበት ፡ የሚገኝ
እንዳንተ ፡ አላይሁም ፡ እንደቃሉ ፡ ታማኝ

፩) አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስራህ ፡ ያስገርማል
ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃልህ ፡ ሰርተሃል
በመገዛት ፡ ያድራል ፡ ፍጥረት ፡ በሥልጣንህ
ታስተዳድራለህ ፡ የለም ፡ የሚያቅትህ

አዝ፦ አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ቃል ፡ ተናገር ፡ እንጂ ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጊዜ ፡ የማይሽረው ፡ ባለበት ፡ የሚገኝ
እንዳንተ ፡ አላይሁም ፡ እንደቃሉ ፡ ታማኝ

፪) ይሁን ፡ ያልከው ፡ ሁሉ ፡ መፈጸሙ ፡ ላይቀር
የሰው ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ማለት ፡ ምንድነው ፡ መሸበር
እኔስ ፡ ለፈቃድህ ፡ ራሴን ፡ ሰጥቻለሁ
አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ እገዛልሃለሁ

አዝ፦ አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ቃል ፡ ተናገር ፡ እንጂ ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጊዜ ፡ የማይሽረው ፡ ባለበት ፡ የሚገኝ
እንዳንተ ፡ አላይሁም ፡ እንደቃሉ ፡ ታማኝ

፫) ምንም ፡ በሌለበት ፡ በምድረበዳው
ታማኝነትህን ፡ አይቻለሁ
ዛሬም ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ገናና ፡ ነህና
ያልከው ፡ ሁሉ ፡ ይሆናል ፡ ሀይል ፡ ያንተ ፡ ነውና

አዝ፦ አንተ ፡ ይሁን ፡ ስትል ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ቃል ፡ ተናገር ፡ እንጂ ፡ የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ (፪x)
ጊዜ ፡ የማይሽረው ፡ ባለበት ፡ የሚገኝ
እንዳንተ ፡ አላይሁም ፡ እንደቃሉ ፡ ታማኝ