ነፍሴ ፡ ሆይ (Nefsie Hoy) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ
አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ
እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ

፩) ኢየሱስ ፡ በፍቅሩ ፡ ወዶሻል
ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ ከአብ ፡ አስታርቆሻል
ታዲያ ፡ ለምን ፡ እረሳሽው ፡ ይህንን ፡ ውለታ
ዘምሪለት ፡ እንጂ፡ ከጥዋት ፡ እስከ ፡ ማታ

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ
አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ
እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ

፪) ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ ሰባብሮ
አንችን ፡ ግን ፡ መርጦሻል ፡ ጠላትን ፡ አባሮ
አትቆጥቢ ፡ ተናገሪ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል
ላመኑት ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ ፡ ይሆናል

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ
አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ
እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ

፫) ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ታመኚ
ባለውለታሽን ፡ እርሱን ፡ አመስግኝ
ምህረቱ ፡ ለዘላለም ፡ አቁሞሻልና
ማዳኑ ፡ ይነገር ፡ ዛሬም ፡ እንደገና

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ
አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ
እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ