ለምልሟል (Lemlemual) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አዝምድረ ፡ በዳዬ ፡ ለምልሟል (፪x)
ኢየሱስ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎልኛል
የዘላለም ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል
የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል

፩) በልቤ ፡ ሲገባ ፡ የየሱሴ ፡ ፍቅሩ
ሕይወቴ ፡ ተገዛ ፡ ጨከነ ፡ ለፍቅሩ
ዛሬ ፡ በደስታ ፡ በአደባባይ ፡ ቆሜ
ያድናል ፡ እላለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ

ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል

፪) ዛሬ ፡ ምን ፡ ይዋጠው ፡ ያክፉ ፡ ጠላቴ
በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
ምክንያትን ፡ ፈላልጐ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢዞረው
እኔ ፡ እንደው ፡ አልገኝ ፡ አጥሬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል

፫) ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ በተነሳው ፡ ጌታ
እኔስ ፡ ተፈወስኩኝ ፡ ከሃጥያት ፡ በሽታ
ዓለም ፡ ሰይጣን ፡ ሥጋ ፡ ዳግም ፡ ላያገኙኝ
በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ አመለጥኩኝ

ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል