አይዞህ (Ayzoh) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው
ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው
የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x)
በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x)

ዙሪያህ ፡ የከበበህ ፡ ሁኔታ ፡ የማይሆን ፡ ቢመስልህ
የምታየው ፡ ሁሉ ፡ ቢዘጋ ፡ ግራ ፡ ቢገባህም
የምትፈራው ፡ ነገር ፡ ላይወርስህ
አይዞህ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልህ

አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው
ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው
የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x)
በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x)

ሰበሰብኩኝ ፡ ስትል ፡ ያያዝከው ፡ከእጅህ ፡ ቢበተንም
ተስፋ ፡ ያረከው ፡ ሁሉ ፡ እርቆ ፡ አልያዝ ፡ ቢልህም
በእግዚአብሔር ፡ ሀሳብ ፡ ላይ ፡ ኑር ፡ እንጂ
አይዞህ ፡ አለህ ፡ ወዳጅ

አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው
ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው
የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x)
በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x)

አልጥልህም ፡ ብሎ ፡ የጠራህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው
ላንተ ፡ ባይመስልህም ፡ አላማው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
ሳትፈራ ፡ ጥቂት ፡ ታገሰው
ጽና ፡ ማጉረምረሙን ፡ ተወው

አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው
ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው
የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x)
በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x)