አለኝ (Alegn) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አለኝ ፡ እኔስ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምታመነው
ዘመን ፡ የማይሽረው ፡ ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

፩) ሁሉ ፡ ሙሉ ፡ ሆኖ ፡ እጥፍ ፡ ቢኖረንም
ለነፍሴ ፡ ጠበቃ ፡ ዋስ ፡ አይሆንልኝም
ለኔ ፡ አለኝ ፡ የምለው ፡ ሁሉ ፡ የማመልከው
አልፋማ ፡ ኦሜጋ ፡ ትልቅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው
ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

፪) ዝና ፡ ከበሬታ ፡ በዚህ ፡ በምድር ፡ ነው
አንድ ፡ ቀን ፡ ሲያበቃ ፡ ሁሉም ፡ አላፊ ፡ ነው
በሰማይ ፡ ቢሆን ፡ ደግሞም ፡በምድር
ለኔስ ፡ ድጋፍ ፡ አለኝ ፡ የማይሰበር

አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው
ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

፫) ሰው ፡ ከማይገምተው ፡ ካልታሰበ ፡ ስፍራ
በፍቅሩ ፡ ማረከኝ ፡ ክብሩን ፡ እንዳወራ
ከሳሾቹን ፡ ሁሉ ፡ እያሳፈረልኝ
አዲስን ፡ ዝማሬ ፡ በአፌ ፡ ጨመረልኝ

አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው
ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)

፬) ለሰይጣን ፡ ሽንገላ ፡ ጆሮዬን ፡ አልሰጥም
ቢያወራ ፡ ቢያወራ ፡ ተስፋዬን ፡ አልጥልም
ቢጐድልም ፡ ቢሞላ ፡ ጌታን ፡ አመልካለሁ
ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ የሚበልጥ ፡ እርሱን ፡ እግኝቻለሁ

አዝ፦ አለልኝ ፡ የምለው
ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)