From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
፩) በሰማይ ፡ የሚታይ ፡ ደመና ፡ ባይኖርም
ንፋስም ፡ ባይኖርም ፡ አይዘንብም ፡ አልልም
የተናገረኝን ፡ አልጠረጥረውም (፪x)
እርሱ ፡ ይሆናል ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ አልልም
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
፪) አላሳልፍ ፡ ብሎ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ቢሞላ
ጉልበቴን ፡ ሊያላላ ፡ አላይም ፡ የኋላ
የጠራኝን ፡ አምላክ ፡ ቃሉን ፡ አምነዋለሁ ፡ እታመነዋለሁ
በእምነት ፡ ተሻግሬ ፡ በድል ፡ እቆማለሁ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
፫) በጉልበቱ ፡ ጽናት ፡ የሚራመደው (፪x)
አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ነው
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ቢያደርግ ፡ ሲያሻው ፡ ቢከለክል (፪x)
በሚሰራው ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትክክል (፪x)
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
፬) አምላክህ ፡ ትቶሃል ፡ ጠላቴ ፡ ቢለኝም
ቢነዘንዘኝም ፡ ይህ ፡ ለኔ ፡ አይገባኝም
ምንም ፡ ቀን ፡ ቢገፋ ፡ ተስፋው ፡ ቢዘገይም
አምላኬ ፡ ያለው ፡ ቃል ፡ መፈጸሙ ፡ አይቀርም
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ አዋቂ ፡ ነው (፪x)
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለአንተም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለአንቺም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለእኔም ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
|