አላፈርኩም (Alaferkum) - ኤፍሬም ፡ ዳኜ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዳኜ
(Ephrem Dagne)

Ephrem Dagne 4.jpg


(4)

አላይም ፡ የኋላ
(Alayem Yehuala)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዳኜ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Dagne)

አዝአላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ

ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ ፍቅርህ ፡ ለይቶኛል
የምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ አኑሮኛል
ታዲያ ፡ከበርኩ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ከሰርኩኝ ፡ እኔ
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ (፬x)
ኢየሱስ ፡ አለ ፡ ከጐኔ

አዝአላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ

ጠላት ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በተነሳ ፡ ጊዜ
ነፍሴን ፡ ሊያስፈራራ ፡ ከቦኝ ፡ በትካዜ
ኢየሱስ ፡ ደረስህልኝ ፡ አሳርፈኽኛል
ስምህ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖ ፡ አስመልጠኸኛል (፬x)
ዛሬ ፡ አድርሰኸኛል

አዝአላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ

ድንቅ ፡ ታምራትህን ፡ ማዳንህን ፡ እያየሁ
ቃል ፡ ኪዳን ፡ አለብኝ ፡ አገለግላለሁ
ገና ፡ የሚበልጥ ፡ አዲስ ፡ ክብር ፡ አለ
ዛሬ ፡ ዓይኔ ፡ ከሚያየው ፡ ከዚህ ፡ የተሻለ (፬x)
ሌላ ፡ ክብር ፡ አለ

አዝአላፈርኩም ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x)
ዛሬም ፡ አለሁኝ ፡ ተደላድዬ