ዝናዬ (zenayie) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(2)

ጸሐፊ (Writer): ገረመው ተፈራ ጮራሞ
(Geremew Tefera Choramo
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ልቤ ሰላም ሲያጣ መከራው ሲበዛ
ወደማን አያለሁ ኢየሱስ ካንተ ሌላ
ልቤ ሰላም ሲያጣ ወጀቡ ሲበዛ
ወደማን አያለሁ የሱስ ካንተ ሌላ

ወየሁ ጠፋሁ ብዬ ሳለቅስ ሳነባ
ብቻዬን ነኝ ብዬ ስቆዝም ስከፋ
የዘላለም አምላክ ኢየሱስ ደረሰልኝ
የልቤን ተናግሮ በሰላም ሂድ አለኝ

አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ይሄ ነው (፪x)

      አዝ፡-ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ
     አንተው ነህና (፪x)

     ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
     ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ
    የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ
    የክብር ሽልማት ዝናዬ

ብኖር ላትጠቀም ሞቼ ላትጎዳ
በደምህ ከፈልከው የሕይወቴን ዕዳ
በደለኛው ልቤን በደምህ ቀድሰህ
ሕይወትን ሸለምከኝ ደህንነት አልብሰህ

ጉድጓዴን ስቆፍር ድንበሬን ልገፋ
ምሕረትህ ገደበኝ ታዝቦ ስገፋ
ነፍሴም ተመለሰች ከርስቷ ግዛት
በመስቀሉ ስራህ በጻድቁ ሞት

አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ይሄ ነው (፪x)

አዝ፡- ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ
     አንተው ነህና (፪x)

     ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
     ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ
     የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ
     የክብር ሽልማት ዝናዬ

የሰጠኝን ላጣ የእጁን ተመኝቼ
ምሕረትን ስጠማ ፍሬዋን በልቼ
የጽድቅን ጥያቄ በልጁ መልሶ
ፈቃዱን አጸና መርገሜን ፈውሶ

     አዝ፡- ዝና ዝናዬ ዝና ዝናዬ
    አንተው ነህና (፪x)

  ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
  ክብር ያሳየኅኝ ዝናዬ
  የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ
  የክብር ሽልማት ዝናዬ


geremewtefera.c@gmail.com