ዘንድሮማ (Zenderoma) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ሕይወቴ ፡ አምሮበታል
ለቅሶ ፡ ማታ ፡ ነበረ ፡ ጠዋት ፡ ደስታ ፡ ሆኗል
ውድቀቴን ፡ ድክመቴን ፡ ለሚፈልገው
ሄዳችሁ ፡ ንገሩት ፡ ዛሬም ፡ እንዳለሁ (፪x)

ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)
አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)

ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x)
ያስለቀሰኝ ፡ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል
ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል (፪x)

ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)
አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)

ህልምን ፡ አየሁ ፡ ብሎ ፡ ላባቱ ፡ ቢያወራ
ወንድሞቹ ፡ ቀንተው ፡ ሸጡት ፡ እንደባሪያ
ዘመን ፡ ሲመጣለት ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ሲወጣ
ሁሉም ፡ ሰገዱለት ፡ በተራ ፡ በተራ (፪x)

ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x)
ያስለቀሰኝ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል
ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል

ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)
አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)

እንዲህ ፡ አልነበረም ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት
የእኛ ፡ ቤት ፡ ሲፈተሽ ፡ የመከራው ፡ ብዛት
የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ በኢየሱስ ፡ ታድሶ
ዛሬም ፡ ይዘመራል ፡ ገደቡ ፡ ተጥሶ (፪x)

ዘንድሮማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)
አሁንማ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል (፪x)

ለእርሱ ፡ ሲመሽበት ፡ ለኔ ፡ ንጋት ፡ ሆኗል (፫x)
ያስለቀሰኝ ፡ ጠላት ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አልቅሷል
ጨለማዬ ፡ በርቶ ፡ ሁሌ ፡ ያዘምረኛል