Ephrem Alemu/Zenayie/Zenayie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ልቤ ፡ ሰላም ፡ ሲያጣ ፡ መከራው ፡ ሲበዛ
ወደማን ፡ አያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ካንተ ፡ ሌላ
ልቤ ፡ ሰላም ፡ ሲያጣ ፡ ወጀቡ ፡ ሲበዛ
ወደማን ፡ አያለሁ ፡ የሱስ ፡ ካንተ ፡ ሌላ

ወየሁ ፡ ጠፋሁ ፡ ብዬ ፡ ሳለቅስ ፡ ሳነባ ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ ስቆዝም ፡ ስከፋ የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ የልቤን ፡ ተናግሮ ፡ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ

አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)
ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ

ብኖር ፡ ላትጠቀም ፡ ሞቼ ፡ ላትጎዳ
በደምህ ፡ ከፈልከው ፡ የሕይወቴን ፡ ዕዳ
በደለኛው ፡ ልቤን ፡ በደምህ ፡ ቀድሰህ
ሕይወትን ፡ ሸለምከኝ ፡ ደህንነት ፡ አልብሰህ

ጉድጓዴን ፡ ስቆፍር ፡ ድንበሬን ፡ ልገፋ ምሕረትህ ፡ ገደበኝ ፡ ታዝቦ ፡ ስገፋ ነፍሴም ፡ ተመለሰች ፡ ከርስቷ ፡ ግዛት በመስቀሉ ፡ ስራህ ፡ በጻድቁ ፡ ሞት

አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ ፡ አወድሃለሁ
ሚገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)
ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ

የሰጠኝን ፡ ላጣ ፡ የእጁን ፡ ተመኝቼ ምሕረትን ፡ ስጠማ ፡ ፍሬዋን ፡ በልቼ የጽድቅን ፡ ጥያቄ ፡ በልጁ ፡ መልሶ ፈቃዱን ፡ አጸና ፡ መርገሜን ፡ ፈውሶ

ዝና ፡ ዝናዬ ፡ ዝና ፡ ዝናዬ
አንተው ፡ ነህና (፪x)

ባገልግሎቴ ፡ ላይ ፡ ዝናዬ ክብር ፡ ያሳየኅኝ ፡ ዝናዬ የማዕረግ ፡ ልብሴ ፡ ዝናዬ የክብር ፡ ሽልማት ፡ ዝናዬ </poem> }}