ትወደኛለህ (Tewedegnaleh) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
አንደምንም ፡ ብዬ ፡ እደርስበታለሁ
የተናገረኝን ፡ ህጄ ፡ እወርሳለሁ
ምን ፡ ሰልፉ ፡ ቢበዛ ፡ ውጊያው ፡ ቢጠነክር
ጸጋው ፡ ይረዳኛል ፡ አይቶልኛል ፡ ክብር

አዝ:-ትወደኛለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያስቀመጥከው (፪x)

ያ ፡ የተስፋ ፡ ቃሌ ፡ የእኔማ
ወሩ ፡ እንደደረሰ ፡ ተሰማ
ሰፈጸም ፡ በእምነት ፡ አይቼ
ልጠብቅ ፡ እጆቼን ፡ ዘርግቼ (፪x)

አዝ:-ትወደኛለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያስቀመጥከው (፪x)

ያመጐናጸፊያ ፡ ወደቀብኝና
ላገልግሎት ፡ ጠራኝ ፡ ጌታ ፡ ለየኝና
በቃ ፡ ላገልግለው ፡ ወገቤን ፡ ታጥቄ
መንፈሱን ፡ ልጠብቅ ፡ የሥጋዬን ፡ ንቄ

አዝ:-ትወደኛለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያስቀመጥከው (፪x)

ክብር ፡ አለ ፡ ብሎ ፡ ሲነግረኝ
ጌታዬን ፡ መለመን ፡ ጀመርኩኝ
ሰፈጸም ፡ በእምነት ፡ አይቼ
ልጠብቅ ፡ እጆቼን ፡ ዘርግቼ (፪x)

አዝ:-ትወደኛለህ ፡ ይህን ፡ አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያስቀመጥከው (፪x)

የነገረን ፡ ትንቢት ፡ አካል ፡ ይለብስና
እኔም ፡ በተራዬ ፡ በሳቅ ፡ እሞላና
በጣር ፡ ክፍሌ ፡ ላይ ፡ እኔም ፡ እቆምና
ኢየሱስ ፡ ይከብራል ፡ በኔ ፡ እንደገና

አልችልም ፡ ብዬም ፡ አልልም
ስንፍናን ፡ በአፌ ፡ አላወራም
ቻይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ቻይ ፡ ነው
አይሆንም ፡ ብዬም ፡ አልልም
ስንፍናን ፡ በአፌ ፡ አላወራም
ቻይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ቻይ ፡ ነው

ያየተስፋ ፡ ቃሌ ፡ የኔማ
ወሩ ፡ እንደደረሰ ፡ ተሰማ
ሰፈጸም ፡ በእምነት ፡ አይቼ
ልጠብቅ ፡ እጆቼን ፡ ዘርግቼ (፪x)

ቻይ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ቻይ ፡ ነው (፬x)