ነገር ፡ አለኝ (Neger Alegn) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
እኔስ ፡ ቃሉን ፡ ስገልጠው ፡ የገረመኝ
የእምነት ፡ አባት ፡ ስላለኝ ፡ ስላለኝ
እኔስ ፡ ቃሉን ፡ ስገልጠው ፡ መንፈስ ፡ ነካኝ
የእምነት ፡ አባት ፡ ስላለኝ ፡ ስላለኝ

ብቻውን ፡ ቆሞ ፡ በአደባባይ
ትወራረደ ፡ ጌታን ፡ ሊታይ
በእሳት ፡ ተገልጦ ፡ አስደንቆታል
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ እኔስ ፡ ገርሞኛል

ቢወዳደሩ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ
ፊት ፡ ብቧጥጡ ፡ በዓል ፡ ቢጠራ
ሳይመጣ ፡ ቀርቶ ፡ ጉድ ፡ አረጋቸው
አንድም ፡ ሳይቀሩ ፡ አስጨረሳቸው

አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር
ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)

አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ አዋጁን ፡ ሽሬ
አመልከዋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ
የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ የማመልከዉ
አዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ ሚያዘምር ፡ ነዉ (፪x)

አኔማ ፡ አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ እኔማ ፡ አዋጁን ፡ ሽሬ
እኔማ ፡ አመልከዋለሁ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፪x)

አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር
ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)

መነሻም ፡ የለኝ ፡ ከተደፋሁ
በዙፋኑ ፡ ሥር ፡ አመሻለሁ
ፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ተባረክ ፡ ስለዉ
ይለቅልኛል ፡ መንፈሱን ፡ ሰማይ ፡ ክፍት ፡ ነዉ (፪x)

እኔማ ፡ ማምለክ ፡ ጀምሬ ፡ እኔማ ፡ መቼ ፡ አቆማለሁ
እኔማ ፡ የነካኝ ፡ ክብር ፡ እኔ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x)

አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር
ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር
ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)