ኩራቴ (Kuratie) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
ቆይቷል ፡ ከገባኝ ፡ እውነቱ
ወንጌል ፡ እንደሆነ ፡ መድሃኒቱ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ማየት ፡ ትቻለሁ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብያለሁ (፪x)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ትቻለሁ
ጌታ ፡ ጌታን ፡ ብያለሁ (፪x)

የዓለም ፡ ትርምስ ፡ ስላልተመቸኝ
ወደ ፡ ጌታ ፡ ፊቴን ፡ አዙርያለሁኝ
ጌታ ፡ ጌታን ፡ ማለት ፡ ያዋጣኛልና
አምላኬን ፡ ልማጸን ፡ መቅደሱ ፡ ልግባና

አዝ:-ለዚህ ፡ ነው ፡ ኩራት ፡ ስላለኝ ፡ አባት
ለዚህ ፡ ነው ፡ ትምክቴ ፡ ስላለኝ ፡ አባት
አባት ፡ ስላለኝ ፡ አባት (፪x)
 
ዓይኖቼ ፡ ተከፍተው ፡ ብድራቴን ፡ ሳይ
በእምነት ፡ እምብ ፡ አልኩኝ ፡ መሾም ፡ ግብጽ ፡ ላይ
የልጅ ፡ ልጅ ፡ ከመባል ፡ ከፈርኦን ፡ ጮማ
መከራን ፡ መረጥኩን ፡ ከእርሱ ፡ ሕዝብ ፡ ጋራ

አዝ:-ለዚህ ፡ ነው ፡ ኩራት ፡ ስላለኝ ፡ አባት
ለዚህ ፡ ነው ፡ ትምክቴ ፡ ስላለኝ ፡ አባት
አባት ፡ ስላለኝ ፡ አባት (፪x)

ቆይቷል ፡ ከገባኝ ፡ እውነቱ
ወንጌል ፡ እንደሆነ ፡ መድሃኒቱ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ማየት ፡ ትቻለሁ
እየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብያለሁ (፪x)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ትቻለሁ
ጌታ ፡ ጌታን ፡ ብያለሁ (፪x)

ቀለለብንና ፡ የዓለም ፡ ነገር
የሰማይ ፡ የሰማይ ፡ ያስብለኝ ፡ ጀመር
መዝገቤ ፡ ተቀምጦ ፡ በበጉ ፡ ከተማ
ልቤም ፡ በዚያ ፡ ቀረ ፡ ምንም ፡ ሳያቅማማ

አዝ:-ለዚህ ፡ ነው ፡ ኩራት ፡ ስላለኝ ፡ አባት
ለዚህ ፡ ነው ፡ ትምክቴ ፡ ስላለኝ ፡ አባት
አባት ፡ ስላለኝ ፡ አባት (፪x)

በጠማማው ፡ ዓለም ፡ ኢየሱስን ፡ ይዤ ፡ (አሃሃሃ) ፡ ኢየሱስን ፡ የዤ
አገለግላለሁ ፡ መቅደሱ ፡ ገብቼ ፡ (አሃሃሃ) ፡ መቅደሱ ፡ ገብቼ
በሚያልፈው ፡ ዓለም ፡ ኢየሱስን ፡ ይዤ ፡ (አሃሃሃ) ፡ ኢየሱስን ፡ የዤ
አገለግላለሁ ፡ መቅደሱ ፡ ገብቼ ፡ (አሃሃሃ) ፡ መቅደሱ ፡ ገብቼ

አዝ:-ለዚህ ፡ ነው ፡ ኩራት ፡ ስላለኝ ፡ አባት
ለዚህ ፡ ነው ፡ ትምክቴ ፡ ስላለኝ ፡ አባት
አባት ፡ ስላለኝ ፡ አባት (፪x)