አኔን ፡ ያየ (Enien Yaye) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋ
በግራ ፡ በቀኝ ፡ እኔን ፡ ቢዋጋ
እጄን ፡ ይዞ ፡ መራኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ

እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ (፪x)
ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ቅጥል ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ

እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ (፪x)
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ (፪x)
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ ሽብሸባ

ይሞታል ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ
አይወርስም ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ (፪x)

አሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነውና (፬x)

አልቆ ፡ ነበረ ፡ የኔ ፡ ጉዳይ
ጌታ ፡ ባይመጣ ፡ ወርዶ ፡ ከላይ (፪x)
አትሞትም ፡ ብሎ ፡ ሞቴን ፡ ሰበረው
የሞትን ፡ መውጊያ ፡ ድል ፡ አደረገው
ድል ፡ አደረገው (፪x)

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ (፪x)
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወግቶ
ወገብ ፡ ተወጋ (፪x)

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋ
በግራ ፡ በቀኝ ፡ እኔን ፡ ቢዋጋ
እጄን ፡ ይዞ ፡ መራኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ

እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ (፪x)
ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ቅጥል ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ

እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ (፪x)
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ (፪x)
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ ሽብሸባ