አይጥልም (Aytelem) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
አዝ:- አይጥልም ፡ አይረሳም ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)
ሰው ፡ ማድረግ ፡ ይችላል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም
ከአመድ ፡ ላይ ፡ ያነሳል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)

አቅም ፡ ጉልበት ፡ አጣሁ ፡ ብሎ ፡ በፍራቻ ፡ ለሚያለቅሰው
ሰው ፡ የሌለው ፡ የተረሳ ፡ እምባው ፡ ምግቡ ፡ የሆነ ፡ ሰው
ተስፋው ፡ ድሉ ፡ ጨልሞበት ፡ የሞቱን ፡ ቀን ፡ ለጠበቀው
ዛሬ ፡ በቃ ፡ የለቅሶ ፡ ቀን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲጐበኘው (፪x)

አዝ:- አይጥልም ፡ አይረሳም ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)
ሰው ፡ ማድረግ ፡ ይችላል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም
ከአመድ ፡ ላይ ፡ ያነሳል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)

በመንፈቀ ፡ ሌሊት ፡ ቀሰቀሰኝ ፡ ዘምር ፡ ብሎ ፡ አዶናይ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ በዝማሬ
በዓለም ፡ ላይ ፡ የሌለ ፡ ሚስጥረኛ ፡ ታማኝ ፡ ትጉ ፡ ደግ ፡ እረኛ
ኢየሱስ ፡ ነዉ ፡ የልቤ ፡ እረኛ (፪x)

ቀን ፡ ሲከፋ ፡ ስጨላልም ፡ አይዞህ ፡ የሚል ፡ ወዳጅ ፡ የለም
በደህና ፡ ቀን ፡ የነበረው ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ ምን ፡ ወሰደዉ
የእኔስ ፡ አባት ፡ ለየት ፡ ይላል ፡ በመከራ ፡ ቀን ፡ ይደርሳል
እርሱን ፡ ታምኖ ፡ ለሚጣራ ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ የሚያኮራ (፪x)

እኔን ፡ ያከበሩ ፡ ይከብራሉ ፡ የናቁኝም ፡ ይናቃሉ
ብሏልና ፡ አባቴ ፡ በቃሉ
እሱን ፡ ላከበረው ፡ ለታመነው ፡ በመንገዱ ፡ ለሚጓዘው
ከቶ ፡ አየውድቅም ፡ ጠንካራ ፡ ግንብ ፡ አለው

አዝ:- አይጥልም ፡ አይረሳም ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)
ሰው ፡ ማድረግ ፡ ይችላል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም
ከአመድ ፡ ላይ ፡ ያነሳል ፡ አይጥልም ፡ አይረሳም (፪x)