አንደኛዬ (Andegnayie) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

 
“አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ አንደኛዬ ፡ ለእኔ
አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ በፍቅር ፡ ምርጫዬ”

አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ አንደኛዬ ፡ ለእኔ
አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ በፍቅር ፡ ምርጫዬ (፪x)

የአንተን ፡ በብዙ ፡ ሺህ ፡ ፍቅርህን ፡ ስላየሁ
እኔስ ፡ ከሰው ፡ ልጅ ፡ ይለያል ፡ እላለሁ
እልፍ ፡ አንደበት ፡ ኖሮኝ ፡ ስላንተ ፡ ባወራ
ከቶ ፡ አይሰለቸንም ፡ ብዘምር ፡ የእንተን ፡ ሥራ

የአንተንስ ፡ ፍቅር ፡ ዘምሬ ፡ አልጨርስ
የአንተንስ ፡ ውለታ ፡ አልረሳውም ፡ ለአፍታ (፪x)

ያልሆነልኝ ፡ ምን ፡ አለ
ያልሰጠኝስ ፡ ምን ፡ አለ
ያልዋለልኝ ፡ ምን ፡ አለ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ተባለ

ዛሬም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ
ነገም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ
ሁሌም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ (አንደኛ)
ይባል ፡ አንደኛ ፡ (ይባል ፡ አንደኛ) ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ

እኔስ ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ንጉሴን ፡ ሾሜያለሁ
አምናና ፡ ካቻምናን ፡ ያለፍኩት ፡ በእርሱ ፡ ነዉ
መቀነት ፡ በወገብ ፡ እንደሚጠብቀው
እኔስ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ተጣብቄያለሁ

ያንተንስ ፡ ፍቅር ፡ ዘምሬ ፡ አልጨርስ
ያንተንስ ፡ ውለታ ፡ አልረሳውም ፡ ለእፍታ (፪x)

ያልሆነልኝ ፡ ምን ፡ አለ
ያልሰጠኝስ ፡ ምን ፡ አለ
ያልዋለልኝ ፡ ምን ፡ አለ
ፍቅር ፡ ነው ፡ ተባለ

አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ አንደኛዬ ፡ ለኔ
አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ በፍቅር ፡ ምርጫዬ (፪x)

በመስቀሉ ፡ ሥራህ ፡ በአራፔ ፡ ፍቅርህ
ወደኸኛል ፡ ጌታ ፡ የኔ ፡ ወግ ፡ የኔ ፡ ክብር
ኪዳን ፡ ገብቶልናል ፡ አልጥልህም ፡ ብሎ
ዛሬም ፡ ይዘምራል ፡ አንደኛ ፡ ተብሎ

አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ (አንደኛ) ፡ አንደኛዬ ፡ ለእኔ
አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ (ለእኔ ፡ አንደኛዬ) ፡ በፍቅር ፡ ምርጫዬ

ዛሬም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ
ነገም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ
ሁሌም ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ
ይባል ፡ አንደኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ

አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ (ለኔ ፡ አንደኛዬ) ፡ አንደኛዬ ፡ ለኔ ፡ (አንደኛ)
አንደኛዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ በፍቅር ፡ ምርጫዬ ፡ (ለእኔ) (፪x)