አዲስ ፡ ዝማሬ (Addis Zemarie) - ኤፍሬም አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 2.png


(2)

ዝናዬ
(Zenayie)

ዓ.ም. (Year): 2009
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ነሁሽጣር ፡ ብዬ ፡ ሰብሬዋለሁ
ያስቸነቀንኝ ፡ ረግቸዋለሁ
ተራራ ፡ መዞር ፡ አበቃ ፡ ዛሬ
ዝማሬ ፡ ሆኗል ፡ አዲስ ፡ ዝማሬ

አዝ:- አዲስ ፡ ዝማሬ ፣ አዲስ ፡ ዝማሬ (፪x)

አላሳልፍ ፡ ያለው ፡ ከፊቴ ፡ የቆመው
ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ ገለል ፡ አደረገው
ቀድሞኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊቴ ፡ ሲወጣ
ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በነኑ ፡ እንደ ፡ ጤዛ

አዝ:- አዲስ ፡ ዝማሬ ፣ አዲስ ፡ ዝማሬ (፪x)

የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ በእሳት ፡ የመለሰው
ዛሬም ፡ በእኔ ፡ ዘመን ፡ የእኔም ፡ ጌታ ፡ ነው
እንኳን ፡ ማንነቱ ፡ ስሙ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
ጠላቴን ፡ ገጥሜ ፡ እበቀለዋለሁ

ሥሙ ፡ የኤልያስ ፡ አምላክ
ሥሙ ፡ የተባለዉ
ሥሙ ፡ በእኔም ፡ ዘመን
ሥሙ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው (፪x)

ሰይጣን ፡ ወደቀ ፡ እንደመብረቅ
ስልቱ ፡ ገብቶኛል ፡ የመዋጋት
አልጨነቅም ፡ ለተሸነፈ
ከእግሬ ፡ በታች ፡ ነው
ስፍራው ፡ ታወቀ

አዝ:- አዲስ ፡ ዝማሬ ፣ አዲስ ፡ ዝማሬ (፪x)

አላሳልፍ ፡ ያለው ፡ ከፊቴ ፡ የቆመው
ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ ገለል ፡ አደረገው
ቀድሞኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊቴ ፡ ሲወጣ
ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በነኑ ፡ እንደ ፡ ጤዛ

አዝ:- አዲስ ፡ ዝማሬ ፣ አዲስ ፡ ዝማሬ (፪x)

የኢናቅ ፡ ልጆች ፡ ረጃጅሞቹ
በአይን ፡ ሲታዩ ፡ አስፈሪዎቹ
በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ሆነው ፡ ሳያቸው
ለካስ ፡ እንደ ፡ እንጀራ ፡ ሚበሉ ፡ ናቸዉ

አዝ:- አዲስ ፡ ዝማሬ ፣ አዲስ ፡ ዝማሬ (፪x)