ሕይወት ፡ ይናገር (Hiwot Yenager) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ርዝመት (Len.): 7:55
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Ephrem Alemu)

አዝሕይወት ፡ ይናገር ፡ እስቲ (፬x)
ወሬ ፡ አይደለም ፡ ምላሳችን
ይናገራል ፡ ሕይወታችን
ሕይወታችን

መመስከር ፡ መጸለይ ፡ ነበር ፡ ሕይወትህ
መንፈሳዊ ፡ ዓለም ፡ ላይ ፡ ከብዶ ፡ ቃላትህ
ዛሬ ፡ ግን ፡ የታለ ፡ የድሮ ፡ ፍቅርህ
ሁሉም ፡ ተቀየረ ፡ አረማመድህ ፡ የታለ ፡ ሕይወትህ

አዝሕይወት ፡ ይናገር ፡ እስቲ (፬x)
ወሬ ፡ አይደለም ፡ ምላሳችን
ይናገራል ፡ ሕይወታችን
ሕይወታችን

ያልኖርንበትን ፡ ተናጋሪ ፡ ተናጋሪ
ውስጣችን ፡ ሲታይ ፡ አሳፋሪ ፡ አሳፋሪ
ለታይታ ፡ መኖር ፡ ቀርቶብን
ጌታን ፡ ያክብረው ፡ ጓዳችን
የአደባባይ ፡ ላይ ፡ ፉከራ
ቤታችን ፡ ይታይ ፡ ሲሰራ

ጽድቅን ፡ ስትከተል ፡ በረከትህ ፡ ይመጣል
መንግሥቱን ፡ ስትሻው ፡ ሌላው ፡ ይጨመራል
ገንዘብን ፡ ግን ፡ መውደድ ፡ የኃጢአት ፡ ስር ፡ ነው
ለሁለት ፡ ጌቶች ፡ መገዛት ፡ አትችልም ፡ ቃሉ ፡ እንደሚለው

አዝሕይወት ፡ ይናገር ፡ እስቲ (፬x)
ወሬ ፡ አይደለም ፡ ምላሳችን
ይናገራል ፡ ሕይወታችን
ሕይወታችን

ሆዳቸው ፡ ሆኖ ፡ አምላካቸው ፡ አምላካቸው
ባሪያ ፡ አድርጐ ፡ ሲገዛቸው ፡ ሲገዛቸው
ቅባቱን ፡ ጥሎ ፡ ነጐደ ፡ የሥጋን ፡ ነገር ፡ ወደደ
ለትውልድ ፡ የሚበቃ ፡ ሰው ፡ ወርቅና ፡ ገንዘብ ፡ ሲያታልለው

አዝሕይወት ፡ ይናገር ፡ እስቲ (፬x)
ወሬ ፡ አይደለም ፡ ምላሳችን
ይናገራል ፡ ሕይወታችን
ሕይወታችን

ክርስቲያን ፡ ነኝ ፡ ካሉ ፡ መኖር ፡ እንደቃሉ
አገልጋይ ፡ ነኝ ፡ ካሉ ፡ መኖር ፡ እንደቃሉ
ክርስትና ፡ ማለት ፡ መስቀል ፡ መሸከም ፡ ነው
እግዚአብሔርን ፡ መስሎ ፡ በሕይወት ፡ መኖር ፡ ነው ፤ ቃሉን ፡ መተግበር ፡ ነው

አዝሕይወት ፡ ይናገር ፡ እስቲ (፬x)
ወሬ ፡ አይደለም ፡ ምላሳችን
ይናገራል ፡ ሕይወታችን
ሕይወታችን