From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ኤፍሬም ፡ አለሙ (Ephrem Alemu)
|
|
ርዝመት (Len.):
|
6:58
|
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች (Other Singles)
|
|
ሌሎች ፡ የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች (Other Albums ፡ by Ephrem Alemu)
|
|
በእኔ ፡ ላይ ፡ ልትሰራ ፡ ጌታ ፡ የወደድከዉ
ምኔ ፡ ደስ ፡ ቢልህ ፡ እንዴት ፡ ብትወደኝ ፡ ነው (፪x)
ምንም ፡ ሳልሰራ ፡ ወደድከኝና
ጌታ ፡ በደምህ ፡ ገዛኸኝና
ከመሬት ፡ ከአፈር ፡ አነሳኸኝ
ሰው ፡ ያላየዉን ፡ አሳየኸኝ
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይገርምም ፡ ወይ
አይደንቅም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይደንቅም ፡ ወይ
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ሲሰራ ፡ መንፈሱ ፡ አሄ
ተራዉ ፡ ሰዉ/ውዳቂው ፡ ከመሬት ፡ ተነስቶ
ሲያመልክህ ፡ እጆቹን ፡ አንስቶን
መንፈስህ ፡ መጥቷል ፡ በጉባኤዉ
የነካዉ ፡ ያመስግነዉ ፡ ዛሬ (፪x)
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይገርምም ፡ ወይ
አይደንቅም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይደንቅም ፡ ወይ
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ሲሰራ ፡ መንፈሱ ፡ አሄ
ከኃጢአቴ ፡ በቀር ፡ አላዉቅም
አንድም ፡ ሚያስመሰግነኝ ፡ የለም
ጌታ ፡ ግን ፡ እጆቹን ፡ ዘርግቶ
ሰራብኝ ፡ አንደበቴን ፡ ከፍቶ (፪x)
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይገርምም ፡ ወይ
አይደንቅም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይደንቅም ፡ ወይ
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ሲሰራ ፡ መንፈሱ ፡ አሄ
የሚሆነዉ ፡ ነገር ፡ ገርሞኛል
ጉባኤዉ ፡ በክብርህ ፡ ተሞልቷል
ዝም ፡ ብዬ ፡ ክብርህን ፡ ሳየዉ
ኦ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ፡ በዬ ፡ እላለሁ (፪x)
በእኔ ፡ ላይ ፡ ልትሰራ ፡ ጌታ ፡ የወደድከዉ
ምኔ ፡ ደስ ፡ ቢልህ ፡ እንዴት ፡ ብትወደኝ ፡ ነው (፪x)
ምንም ፡ ሳልሰራ ፡ ወደድከኝና
ጌታ ፡ በደምህ ፡ ገዛኸኝና
ከመሬት ፡ ከአፈር ፡ አነሳኸኝ
ሰው ፡ ያላየዉን ፡ አሳየኸኝ
አይገርምም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይገርምም ፡ ወይ
አይደንቅም ፡ ወይ ፡ ኧረ ፡ አይደንቅም ፡ ወይ
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ሲሰራ ፡ መንፈሱ ፡ አሄ
|