ልዘምርለት (Lezemerelet) - ኤፍሬም ፡ እና ፡ ኢዮአብ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ እና ፡ ኢዮአብ
(Ephrem Alemu)

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ለማን ፡ አዳልቶ
(Leman Adalto)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ እና ፡ ኢዮአብ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ጠብቆኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ያለሁት ፡ ከጠላቴ ፡ ዛቻ
መቼ ፡ እወጣው ፡ ነበር ፡ ለብቻዬ ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ
በጐኔ ፡ ሳይርቀኝ ፡ ሳይለየኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
መንገዴን ፡ አንቅቶ ፡ ጀምሬያለሁ ፡ የሰላምን ፡ ጉዞ

በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ
በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x)

ብዘምርለት ፡ መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት (፬x)
ካረገው ፡ ጋራ ፡ መች ፡ ሊወዳደር ፡ የእኔ ፡ መዘመር

በእስራኤል/በኤፍሬም ፡ ላይ ፡ ሟርትም ፡ አይሰራ
ድንጋጤም ፡ ቤቱ ፡ አይገባ
እግዚአብሔር ፡ ቅጥር ፡ ሆኖታል
በከፍታ ፡ ያዘምረዋል (፬x)

እንደ ፡ ትላንትናው ፡ መስሎ ፡ ጠላት ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ሲመጣ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ቤቴ ፡ አለ ፡ ኢየሱሴ ፡ የሰላም ፡ አለቃ
ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ በጉበእኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
አልቻለም ፡ ጠላቴ ፡ እንደድሮ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሊጠጋ

በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ
በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x)

በእስራኤል/በኤፍሬም ፡ ላይ ፡ ሟርትም ፡ አይሰራ
ድንጋጤም ፡ ቤቱ ፡ አይገባ
እግዚአብሔር ፡ ቅጥር ፡ ሆኖታል
በከፍታ ፡ ያዘምረዋል (፬x)

ትጠፋለህ ፡ ብሎ ፡ የደገመው ፡ ጠላቴ ፡ የታለ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አለሁኝ ፡ በሕይወቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለለ
በአንዳች ፡ አልጨነቅ ፡ አልሸበር ፡ ለነገም ፡ አልፈራ
በአንድ ፡ የመጣው ፡ ጠላት ፡ ይበተናል ፡ በሰባት ፡ ጐዳና

በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ
በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ
በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x)

ብዘምርለት ፡ መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት (፫x)
ካረገው ፡ ጋራ ፡ መች ፡ ሊወዳደር ፡ የእኔ ፡ መዘመር