የጌታ ፡ ልጅ (Yegieta Lej) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

የጌታ ፡ የጌታ ፡ ልጅ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ቀና ፡ በል ፡ እንጂ
የአባቴ ፡ የአምላኬ ፡ ልጅ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ኮራ ፡ በል ፡ እንጂ

ጠላት ፡ ሲቆዝም ፡ ያቀርቅር ፡ እንጂ
ቀና ፡ ቀና ፡ በል ፡ የጌታ ፡ ልጅ
እርሱን ፡ ለፈራው ፡ ላከበረው
እስከ ፡ ሺህ ፡ ትውልድ ፡ በረከት ፡ ነው
ጌታን ፡ ተማምኖ ፡ የለም ፡ ዝምታ
በእርግጥ ፡ ተሰብሯል ፡ ይመለክ ፡ ጌታ

ከዚህ ፡ በፊት ፡ የለመድኩት
የጠየኩት ፡ ያሳየሁት ፡ ነገር (፪x)
ዞሮ ፡ ገባ ፡ እጄ ፡ ገባ
አልቀረብኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ነገር
ዙፋኑ ፡ ስር ፡ መቅደሱ ፡ ስር
ማደሪያው ፡ ስር ፡ ስለምነው ፡ ውዬ (፪x)
አላፈርኩም ፡ አልከሰርኩም ፡
ተሳካልኝ ፡ ጌታ ፡ ጌታን ፡ ብዬ (፪x)

ብዬማ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ብዬ
ብዬማ ፡ ታለምአልኜ
ብዬማ ፡ ነገር ፡ ተሳካ
ብዬማ ፡ እርሱን ፡ ለምኜ

የኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ
ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ
ለክብሩ ፡ የሚሆን ፡ አምጡ ፡ ምሥጋና
እስቲ ፡ ጨምሩለት ፡ ቅዱስ ፡ ነውና

ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ የምን ፡ ዝምታ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ውዬ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ይነጋ

የጌታ ፡ የጌታ ፡ ልጅ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ቀና ፡ በል ፡ እንጂ
የአባቴ ፡ የአምላኬ ፡ ልጅ
የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ኮራ ፡ በል ፡ እንጂ

መንግሥተ ፡ ሠማይ ፡ የጀግና ፡ አገር
የእኛም ፡ አገር ፡ ነች ፡ በዚያ ፡ እንድንኖር
በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በላይ ፡ ደስታ
ትልቅ ፡ ዕድል ፡ ነው ፡ መሆን ፡ የጌታ
አክሊል ፡ ያገኛል ፡ ድል ፡ ያነሳው
ለእግዚአብሔር ፡ ኖሮ ፡ የጨረሰው

ኢየሱሴን ፡ ተቀብሎ
. (1) . ጌታ ፡ ንጉሥ ፡ ያደረገውን ፡ ሰውን
እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም ፡ የታደለ
ምስጉን ፡ ትውልድ ፡ ከሞት ፡ ያዳነው ፡ ሰው
ውኃው ፡ ተባርኮለት
ደዌ ፡ ችግር ፡ ተወግዶለት ፡ ሞትን
ተዘልሎ ፡ ተቀምጧል
እንደ ፡ አንበሳ ፡ አርፏል ፡ በድፍረት ፡ ሕይወት

እርሱማ ፡ ያመስግነው
እርሱማ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነው
እርሱማ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ
እርሱማ ፡ ሊዘምረው

የኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ
ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ
ለክብሩ ፡ የሚሆን ፡ አምጡ ፡ ምሥጋና
እስቲ ፡ ጨምሩለት ፡ ቅዱስ ፡ ነውና

ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ የምን ፡ ዝምታ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ውዬ
ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ይነጋ

እርሱማ ፡ ያመስግነው
እርሱማ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነው
እርሱማ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ
እርሱማ ፡ ሊዘምረው