ተይ ፡ ነፍሴ (Tey Nefsie) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

አዝ፦ ተይ ፡ ነፍሴ
የአምላክሽን ፡ ቃል ፡ ስሚና
ግራ ፡ ቀኙን ፡ ተይውና
ኋላ ፡ ደግሞ ፡ እንዳይቆጭሽ
ከአምላክሽ ፡ ጋር ፡ ተጣልተሽ
እርሱ ፡ ነው ፡ ሚረባሽን ፡ ሚያውቅልሽ
ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፡ የሚረባሽን

አሃሃ ፡ አምላክሽ ፡ አለ ፣ አሃሃ ፡ ሚያስብልሽ
አሃሃ ፡ ግራና ፡ ቀኙን ፣ አሃሃ ፡ ምን ፡ አሳየሽ
አሃሃ ፡ እርሱስ ፡ ስለአንቺ ፣ አሃሃ ፡ ቆስሏልና????
አሃሃ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፣ አሃሃ ፡ አይጠቅምምና

ኤሄ ፡ ሞልቶ ፡ ላይሞላ
ኤሄ ፡ ለዓለም ፡ ነገር
ነፍሴ ፡ አትጨነቂ ፡ የቀረው ፡ ይቅር
ኤሄ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ኤሄ ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
ነፍሴ ፡ ቃሉ ፡ ይሻላል ፡ የእርሱ ፡ የአንደበቱ

እኔ ፡ ደግሞ ፡ ወይ ፡ ለራሴ
ቀን ፡ አስቦ??? ፡ ለክብር ፡ ነፍሴ
የሰጠኀኝ ፡ ፈራሽ ፡ ሥጋዬ
ላይሆነኝ ፡ መከበሪያዬ
አባትዬ ፡ ባክህ ፡ አደራ
በዘመኔ ፡ ስራህን ፡ ልስራ
አስከብሬህ ፡ ልኑር ፡ ለክብርህ
ስምህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዲጠራ

አዝ፦ ተይ ፡ ነፍሴ
የአምላክሽን ፡ ቃል ፡ ስሚና
ግራ ፡ ቀኙን ፡ ተይውና
ኋላ ፡ ደግሞ ፡ እንዳይቆጭሽ
ከአምላክሽ ፡ ጋር ፡ ተጣልተሽ
እርሱ ፡ ነው ፡ ሚረባሽን ፡ ሚያውቅልሽ
ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፡ የሚረባሽን

አሃሃ ፡ አታስጨንቂኝ ፣ አሃሃ ፡ አታውኪኝ
አሃሃ ፡ ወዲህና ፡ ወዲያ ፣ አሃሃ ፡ አትበይቢኝ
አሃሃ ፡ የዓለም ፡ ብልጭልጭ ፣ አሃሃ ፡ መልኩ ፡ ውበቱ
አሃሃ ፡ ሁሉም ፡ ጠፊ ፡ ነው ፣ አሃሃ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ

ኤሄ ፡ ኀጢአት ፡ ብትሰሪ
ኤሄ ፡ ትሞቻለሽ
ነፍሴ ፡ ጽድቅን ፡ ብትሰሪ
በሕይወት ፡ ትኖሪያለሽ
ኤሄ ፡ እንዳያዝንብሽ
ኤሄ ፡ የሞተልሽን
ነፍሴ ፡ ለጽድቅ ፡ ንቂ
በሕይወት ፡ ለሚያኖርሽን

ሥጋ ፡ ነቅቶ ፡ መንፈስ ፡ ቢደክም
መንፈስ ፡ ነቅቶ ፡ ሥጋ ፡ ሲደክም
ለበረታው ፡ ላሸነፈው ፡ ብትወግኚ ፡ ለበለጠው
ነፍሴ ፡ ዕውቀት ፡ ፍቃድ ፡ አለሽ
ተገዢለት ፡ ለታደገሽ
ለግዚአብሄር ፡ ለስሙ ፡ ኑሪ
በሰማይ ፡ ቤት ፡ ፊቱ ፡ እንዳታፍሪ