ትርፌማ ፡ ቅባት ፡ ነው (Terfiema Qebat New) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ሥምህ ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል
ሁሌ ፡ ስጠራው ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
የትኛው ፡ ሥም ፡ ነው ፡ የተወደደው
ጠዋት ፡ ተወርቶ ፡ ማታ ፡ የሚወርደው
እንዳየነው

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሥሙ ፡ ይለያል
ሁሌ ፡ ስጠራው ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ጠረነ ፡ ልዩ ፡ ማዕዛ ፡ ያለው
የአባትዬ ፡ ሥም ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ነው
እንደ ፡ ማር

እንደ ፡ ማር ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ ማር (፬x)

እኔስ ፡ ቆርጫለሁ ፡ ለጌታ ፡ ዘንድሮ
ሕይወት ፡ ተገለጠ ፡ በራልኝ ፡ በቶሎ
ዋጋዬን ፡ ተምኜ ፡ ስለወጣሁኝ
እመቅደሱ ፡ ደጃፍ ፡ ወስዳችሁ ፡ ጣሉኝ

ትርፌማ ፡ ቅባት ፡ ነው ፡ ቅባት ፡ በመንገዴ
ያገኘኛል ፡ አልኩኝ ፡ ያየኛል ፡ አባቴ
ዋጋዬን ፡ ተምኜው ፡ ስለወጣሁኝ
እመቅደሱ ፡ ደጃፍ ፡ ወስዳችሁ ፡ ጣሉኝ (፫x)

አሄ ፡ ኦሆ

አርዶ ፡ የወጣ ፡ ሰው ፡ ከቶ ፡ አይመለስም
ጌልጌላ ፡ ተነስቶ ፡ ቤቴል ፡ ላይ ፡ አይቆምም
እያሪኮን ፡ አልፎ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ይዘልቃል
እጥፍ ፡ መንፈስ ፡ ይዞ ፡ በክብር ፡ ይመለሳል

በኤልያስ ፡ እጅ ፡ ላይ ፡ ውኃ ፡ የሚያፈሰው
አስራ ፡ ሁለት ፡ ጥማድ ፡ በሬ ፡ አረደው
በሕያው ፡ ልብሱ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የተከተለው
ሞኝ ፡ ሆኖ ፡ አይደለም ፡ ክብር ፡ አይቶ ፡ ነው
ቅባት ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ አይቶ ፡ ነው

ጌልጌላ ፡ ሸለፈትክ ፡ የተገረዘው
ቤቴል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ የተጸለየው
እያሪኮም ፡ ይናድ ፡ በጩኸት ፡ ይፍረስ
ዮርዳኖስ ፡ ልጠመቅ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ

አባናና ፡ ፋርፋን ፡ አልል ፡ እንደ ፡ ሰው
ዮርዳኖስ ፡ ይበልጣል ፡ የደፈረሰው
ብቅ ፡ ትልቅ ፡ ብዬል ፡ ከለምጽ ፡ እነጻለሁ
አንተ ፡ ያልከኝ ፡ ቦታ ፡ ፈውስ ፡ አገኛለሁ (፪x)
መዳን ፡ አገኛለሁ

ዘመኔ ፡ እንደ ፡ ሻማ ፡ እንደ ፡ ጧፍ ፡ ቢነድ
ያንስበታል ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ይበዛበት
እርሱማ ፡ ተዋርዶ ፡ በሞቱ ፡ አክብሮኝ
ለኢየሱሴ ፡ ኖሬ ፡ እስቲ ፡ ይለይልኝ

አሸፈተው ፡ ልቤን ፡ ኢየሱስን ፡ ወዶ
የሠማይ ፡ አስባለኝ ፡ የምድሩን ፡ አስንቆ
ልቤ ፡ ትዝታዬም ፡ እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረና
ሁሉንም ፡ አሳቀኝ ፡ የእርሱ ፡ በለጠና
ክብር ፡ በለጠና ፡ ቅባት ፡ በለጠና

ሞኝ ፡ ነህ ፡ ይሉኛል ፡ የታል ፡ ሞኝነቴ
አተረፈኩኝ ፡ እንጂ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጉዳቴ
ኢየሱስን ፡ ይዤ ፡ እኔስ ፡ አትርፊያለሁ
ምድር ፡ ተቀምጬ ፡ ቤቴ ፡ በሠማይ ፡ ነው

ይኸውልህ ፡ ልቤን ፡ እንካ ፡ ውሰደው
አንተ ፡ ጋር ፡ ይቀመጥ ፡ የእኔ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ ሰብስቤ ፡ ለአንተ ፡ ሰጠሁና
አንተን ፡ አንተን ፡ አልኩኝ ፡ የአንተ ፡ በለጠና
መንፈስ ፡ በለጠና ፡ ቅባት ፡ በለጠና