ሲጀምር ፡ በቅባት (Sijemer Beqebat) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ሲጀምር ፡ በቅባት ፡ ሲያልቅም ፡ በቅባት
እግዚአብሔር ፡ ስላለ ፡ የኃያላን ፡ አባት
አይወድቁም ፡ አንወድቅም ፡ ከዛሬ ፡ ጀምሮ
ገና ፡ ይነሳሉ ፡ ቅባቱን ፡ ጨምሩ ፡ መንፈሱን ፡ ጨምሩ

ጨመረብኝ ፡ ቅባቱ ፡ ጨመረብኝ
ወረደብኝ ፡ መንፈሱ ፡ ፈሰሰብኝ
እግዚአብሔር ፡ በክብር ፡ በበቀል ፡ አስነሳኝ
ጨመረብኝ ፡ ቅባቱ ፡ ጨመረብጭ
በአዳዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በምሥጋና ፡ ሞላኝ
ጨመረብኝ ፡ ቅባቱ ፡ ጨመረብጭ
እግዚአብሔር ፡ በክብር ፡ በበቀል ፡ አስነሳኝ
ጨመረብኝ ፡ ቅባቱ ፡ ጨመረብጭ
በአዳዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በምሥጋና ፡ ሞላኝ

ኤልያስን ፡ ሳይቀር ፡ ያስፈራራችው
ናቦትን በርስቱ ፡ በርስቱ ፡ ያስገደለችው (፪x)
አረፍን ፡ ዘንድሮ ፡ እዩ ፡ ተቀብቷል
ኤልዛቤልን ፡ ከላይ ፡ ይፈጠፍጣታል ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል

ጉድ ፡ ፈላባት ፡ ኤልዛቤል ፡ ጉድ ፡ ፈላባት

ጉድ ፡ ፈላባት ፡ ኤልዛቤል ፡ ጉድ ፡ ፈላባት
እንዲህ ፡ አትቀጥልም ፡ እንዳማረባት
ጉድ ፡ ፈላባት ፡ ኤልዛቤል ፡ ጉድ ፡ ፈላባት
ድንገት ፡ ሳታስበው ፡ እዩ ፡ ተነሳባት (፪x) [1]

ዓይኑ ፡ አረፈብኝ ፡ ወዳጄ (፬x)
ከሰዉ ፡ መሃል ፡ ሲያደላ ፡ ለእኔ ፡ አየሁት ፡ በዐይኔ (፪x)
ተሸክሞኛል ፡ በንስር ፡ ክንፍ
እንደ ፡ እናትም ፡ አባትም ፡ ሆነልኝ (፪x) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የእንደገና ፡ አምላክ ፡ እንደገናዬ
በእጅህ ፡ መዳፍ ፡ ቀረጽከኝ (፪x) ፡ ሆንከኝ ፡ ጌታዬ

ጌታዬ (፪x) (ባለውለታዬ)
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (ሆንከኝ ፡ ጥላዬ)

ጐልያድ ፡ ሚባለው ፡ የውጊያ ፡ ጦረኛ
አርባ ፡ ቅን ፡ ሲፎክር ፡ ህዝቡን ፡ አልስተኛም (፪x)
ይፎክር ፡ ዝም ፡ በሉት ፡ ዳዊት ፡ እስኪመጣ
በጠጠር ፡ ይወድቃል ፡ የማታ ፡ የማታን ፡ የማታ ፡ የማታ [2]

የማታ ፡ የማታ ፡ ድሉ ፡ የጌታ ፡ ነው ፡ የማታ ፡ የማታ (፪x)
ተሸክሞኛል ፡ በንስር ፡ ክንፍ
እንደ ፡ እናትም ፡ አባትም ፡ ሆነልኝ (፪x) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የእንደገና ፡ አምላክ ፡ እንደገናዬ
በእጅህ ፡ መዳፍ ፡ ቀረጽከኝ (፪x) ፡ ሆንከኝ ፡ ጌታዬ

ጌታዬ (፪x) (ባለውለታዬ)

  1. ፪ ነገሥት ፱ ፡ ፴ - ፴፭ (2 Kings 9:30-35)
  2. ፩ ሳሙኤል ፲፯ ፡ ፰ - ፶፩ (1 Samuel 17:8-51)