መልሰኝ (Melesegn) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

እረጅሙን ፡ ጐዳና ፡ በጽድቅ ፡ እንዳልሄድኩኝ
አንተን ፡ እንዳላሳዝን ፡ ፊትህ ፡ እንደማልኩኝ
ዛሬ ፡ ምነው ፡ ጠፋኝ ፡ አቅም ፡ አጠረኝኝ

እኔ ፡ ነኝ ፡ ጥፋተኛ ፡ እኔን ፡ እኔን ፡ ማረኝ
ዕንቁዬን ፡ ሜዳ ፡ ጥዬው ፡ ብቻዬን ፡ ቀረሁኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መልሰኝ ፡ ምህረት ፡ አድርግልኝ

አዝ፦ መልሰኝ ፡ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወዳስተማርከኝ
መልሰኝ ፡ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወደነገርከኝ
አንተን ፡ ተጣልቼ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ከአንተ ፡ ተስማምቼ ፡ እኔስ ፡ እኖራለሁ

ስታበይ ፡ ገሥጸኝ ፡፡ ሳጠፋ ፡ ቅጣኝ
መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ
አንተ ፡ ዝም ፡ ካልከኝ ፡ ምንስ ፡ ይውጠኛል
የአንተ ፡ ዝምታ ፡ እኮ ፡ አፍ ፡ አለው ፡ ያወራል

ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ የነገርከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ያልከኝ
እኔስ ፡ ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ እንዳልከኝ (፪x)

ብዙ ፡ የለፋሁበት ፡ ያከማቸሁት ፡ ሃብቴ
ከእጄ ፡ ላይ ፡ ተበተነ ፡ ሳላውቀው ፡ ከጥማቴ
የተቀደስኩለት ፡ ከዳኝ ፡ ማንነቴ
አወይ ፡ አለመታዘዝ ፡ አሻፈረኝ ፡ ማለቴ
አይረባህም ፡ ስትለኝ ፡ አንተን ፡ አለመስማቴ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ገብቶኛል ፡ አድሰኝ፡ አባቴ

አዝ፦ መልሰኝ ፡ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወዳስተማርከኝ
መልሰኝ ፡ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወደነገርከኝ
አንተን ፡ ተጣልቼ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ከአንተ ፡ ተስማምቼ ፡ እኔስ ፡ እኖራለሁ

ጴጥሮስ፡ ሓዋርያው ፡ አልክድህም ፡ ያለው
ዶሮ ፡ ሳይጮህ ፡ በፊት ፡ ሶስት ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ የካደው
ነገር ፡ ግን ፡ ምህረትህ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ
አስበህ ፡ ለወጥከው ፡ ሰው ፡ አደረከው ፡ ጌታ

ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ የነገርከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ያልከኝ
እኔስ ፡ ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ እንዳልከኝ (፪x)