ክንዱ ፡ ነው (Kendu New) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

አዝ፦ ክንዱ ፡ ነው ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው
ጣቱ ፡ ነው ፡ ነገሬን ፡ የቀያየረው (፪x)

አይቻለሁ ፡ በአንተ
ሸለቆው ፡ ውኃ ሲሞላ
ጌታ ፡ ስትሆነኝ ፡ ከለላ (፪x)

አንገት ፡ እንድደፋ ፡ እንዳቀረቅር
ከሰው ፡ በታችን ፡ ሆኜ ፡ ነበር ፡ ምኞቱ
ጠላቴማ ፡ ሰው ፡ ለማድረግ ፡ ከንቱ ፡ አወይ ፡ ልፋቱ
የማመልከው ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
እንደገና ፡ አነሳኝ ፡ ዳግም ፡ አቆመኝ

ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እኮ ፡ ማነው ፡ ማነው
እሃሃሃ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኮ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው
(፪x)

አዝ፦ ክንዱ ፡ ነው ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው
ጣቱ ፡ ነው ፡ ነገሬን ፡ የቀያየረው (፪x)

አይቻለሁ ፡ በአንተ
ሸለቆው ፡ ውኃ ሲሞላ
ጌታ ፡ ስትሆነኝ ፡ ከለላ (፪x)

በዚያ ፡ በጭንቅ ፡ ቀን ፡ በቁርጥ ፡ ጊዜ ፡ በመከራ ፡ ሰዓት
ከጐኔ ፡ የሚቆም ፡ አይዞህ ፡ የሚለኝ ፡ አጋዥ ፡ ባጣሁበት
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲመጣ
ጉልበቴም ፡ ከፍ ፡ አለልኝ ፡ አቅሜም ፡ በረታ

ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ማነው
ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እኮ ፡ ማነው ፡ ማነው
እሃሃሃ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኮ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የደረሰው
(፪x)