ክብራችን ፡ አንተ (Kebrachen Ante) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ክብራችን ፡ አንተ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጣችን
ውበታችን ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አባታችን
በጨለማ ፡ ላይ ፡ የምታበራ
የንጋት ፡ ኮከብ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ከፍ ፡ በል

የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ገዳይ
የዳዊት ፡ ዘር ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ኤልሻዳይ
ሲኦልን ፡ ድል ፡ ነስተህ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ
ዘራችን ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ዘማሪ :ከፍ በል

የአንተ ፡ በመሆኔ ፡ ኮራሁኝ ፡ እኔ
የእኔ ፡ ነህ ፡ ሲለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ)
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ
ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው
አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ምድር ፡ አልቻለችም ፡ አለቃዋን ፡ ይዛ
መልሳ ፡ ተፋችው ፡ ፈጣሪዋን ፡ ታዛ
ዓለምና ፡ ሰይጣን ፡ ሲዖል ፡ ያልቻለው
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው

አቻ ፡ የሌለው ፡ ወደር ፡ የሌለው
ኢየሱስዬ ፡ ብቻ ፡ ሞት ፡ ያልበገረው
አቻ ፡ የሌለው ፡ ወደር ፡ የሌለው (፪x)

አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ)
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ
ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው
አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

እግሩ ፡ እንደ ፡ ጋለ ፡ ናስ ፡ ዐይኖቹ ፡ ነበልባል ፡ ነው
እርሱን ፡ ተመልክቶ ፡ የሚቆም ፡ ሰው ፡ ማነው
ስንቱ ፡ ጀግና ፡ ሞቶ ፡ መቃብር ፡ ሲቀር
ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ አርጓል ፡ በክብር

ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነው ፡ ያለ ፡ የነበረ
ወደፊትም ፡ ይኖራል ፡ ገና ፡ እየከበረ
እየተከበረ ፡ ገና ፡ እየከበረ (፪x)

ክብራችን ፡ አንተ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጣችን
ውበታችን ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አባታችን
በጨለማ ፡ ላይ ፡ የምታበራ
የንጋት ፡ ኮከብ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ከፍ ፡ በል

የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ገዳይ
የዳዊት ፡ ዘር ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ኤልሻዳይ
ሲኦልን ፡ ድል ፡ ነስተህ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ
ዘራችን ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ዘማሪ : ከፍ:በል

የአንተ ፡ በመሆኔ ፡ ኮራሁኝ ፡ እኔ
የእኔ ፡ ነህ ፡ ሲለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ)
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ
ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው
አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢ ፡ ሲፎክር ፡ ሲያቅራራ
ገደልኩት ፡ ቀበርኩት ፡ እያለ ፡ ሲያወራ
በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ጠላቴም ፡ ወደቀ ፡ በይሁዳ ፡ አንበሳ

ሰባቱን ፡ ማህተም ፡ ቋጠሮን ፡ የፈታ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፫x)
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፣ የይሁድ ፡ አንበሳ (፪x)

ለክብሩ (ሆ) ፡ ለኃይሉ (ሆ)
ቢዘመር (ሆ) ፡ ለስሙ (ሆ)
ቢወራ ፡ በምድር ፡ አይበቃም ፡ ለእግዚአብሔር
ለእግዚአብሔር (፫x) ፡ አለኝ ፡ ዘምር
ለእግዚአብሔር (፫x) ፡ አለኝ ፡ ዘምር

"ሃሌሉያ ፡ እሰይ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ አቻ ፡ የለውም"