ከአንተ ፡ ጋር (Keante Gar) - ኤፍሬም ፡ አለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ አለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ያለ ፡ አንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ብቻዬን ፡ አያምርብኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር (፪x)

በንጉሥ ፡ ጮማ ፡ ከኖሩ ፡ ቆሎ ፡ ቆርጥመው ፡ ያደሩ
አስር ፡ እጅ ፡ አማረባቸው ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ የወገኑ
በምድር ፡ ተጨምጭቦልኝ ፡ በሰማይ ፡ ከምታፍርብኝ
ይቅርብኝ ፡ ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ብቻ ፡ ልኑር

መራብን ፡ አውቃለሁ ፡ መጥገብን
ማግኘትን ፡ አውቃለሁ ፡ ማጣትን
እኔ ፡ ማይሆንልኝ ፡ ማያምርብኝ
ያላንተ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ የታውቅክልኝ
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
(፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ያለ ፡ አንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ብቻዬን ፡ አያምርብኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልጠጣ ፡ ያረካኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር

ቢቃጠል ፡ ወጣትነቴ ፡ ቢነድም ፡ ለአንተ ፡ ጉልበቴ
ቢቀናም ፡ ክፉ ፡ ጠላቴ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አባቴ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ዕድሜ ፡ ሰንቃላ ፡ ሰማንያ ፡ አመት ፡ የማይሞላ
ድካም ፡ ነው ፡ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ አልሆንም ፡ እኔስ ፡ ተላላ

ሺህ ፡ ዓመት ፡ አልኖርም ፡ በምድር
እንደእንፋሎት ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ዘመን
በቃ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ልኑርና
ዘመኔን ፡ ጨርሰው ፡ ጌታ ፡ ቀድስና
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
(፪x)

ሙሴ ፡ አይቶ ፡ ብድራቱን ፡ የልጅ ፡ ልጅ ፡ ንግስናውን
ንቆታል ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብሎ ፡ አልጋውን ፡ ክብሩን ፡ ተምኖ
ኧረ ፡ ለእኔ ፡ ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ብዬ ፡ ምኖረው
እንኳን ፡ አገልጋይ ፡ ሆኜ ፡ ይበቃል ፡ ባሪያ ፡ መባሌ

የእኔ ፡ መጨረሻ ፡ ጥግ ፡ እርካታዬ
መገኘትህ ፡ ሲኖር ፡ በቤት ፡ በጓዳዬ
ያን ፡ ጊዜ ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ኧረካለሁ
ፊትህን ፡ እያየሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ እጠግባለሁ

ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ባልጠጣ ፡ ያረካኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር