ካልባረከኝ (Kalbarekegn) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

በረከት ፡ ፍለጋን ፡ ስንከራተት
እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ አይ ፡ ስዋትት
ዛሬ ፡ ግን ፡ ገብቶኝ ፡ መጥቻለሁ
አንተን ፡ ከአገኘሁ ፡ ምን ፡ እሻለሁ

አዝካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ስሜን ፡ ቀይረህ ፡ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ልጄ ፡ ነህ ፡ ብለህ ፡ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)

ሓሩሩ ፡ ኩሩ ፡ አቃጠለኝ
ደሞዜን ፡ ስንቴ ፡ ቀየረብኝ
ሽቅብ ፡ ስወጣ ፡ ቁልቁል ፡ ስወርድ
ዘመኔን ፡ ፈጀሁ ፡ በላባ ፡ ቤት

ቆይ ፡ ምን ፡ ያደርጋል ፡ ሃብት ፡ ቢበዛ
አንተ ፡ ከሌለህ ፡ ካልሆንከኝ ፡ ቤዛ
ሌሊቱ ፡ አቅላልቷል ፡ ሊነጋብኝ
እኔ ፡ አለቅህም ፡ ካልባረከኝ

ጌታ ፡ አድነኝ ፡ ለውጠኝ
ማለቴን ፡ አልተውም ፡ እስክትለውጠኝ
ጌታ ፡ አድነኝ ፡ ለውጠኝ
ጸሎቴን ፡ አልተውም ፡ እስክትለውጠኝ

በረከት ፡ ፍለጋን ፡ ስንከራተት
እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ አይ ፡ ስዋትት
ዛሬ ፡ ግን ፡ ገብቶኝ ፡ መጥቻለሁ
አንተን ፡ ከአገኘሁ ፡ ወርሻለሁ???

አዝካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ስሜን ፡ ቀይረህ ፡ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ልጄ ፡ ነህ ፡ ብለህ ፡ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)

የቅድስናን ፡ የጽድቅን ፡ ኑሮ
መኖር ፡ ፈልጌ ፡ ከአምናው ፡ ዘንድሮ
አመታት ፡ ዘመን ፡ ወሰደብኝ
መቼ ፡ ነው ፡ መጥተህ ፡ ምትቀይረኝ

እኔ ፡ አልፈልግም ፡ እንደዚህ ፡ ኑሮ
ተራራ ፡ መዞር ፡ አመታት ፡ ቆጥሮ
እስቲ ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ፈቀቅ ፡ አርገኝ
በክብርህ ፡ ልኑር ፡ አሳርፈኝ

ጌታ ፡ አድነኝ ፡ ለውጠኝ
ማለቴን ፡ አልተውም ፡ እስክትለውጠኝ
ጌታ ፡ አድነኝ ፡ ለውጠኝ
ጸሎቴን ፡ አልተውም ፡ እስክትለውጠኝ

አዝካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ስሜን ፡ ቀይረህ ፡ ካልቀባኀኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)
ልጄ ፡ ነህ ፡ ብለህ ፡ ካለወጥከኝ
ካልባረከኝ ፡ አለቅህም ፣ ካልዳሰስከኝ ፡ አልተውህም (፪x)