አልችልበትም (Alchelebetem) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ስለማልችል ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር
አትሂድብኝ ፡ ባክህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
እኔስ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ አልችልምና
ችላ ፡ አትበለኝ ፡ ክብሬን ፡ ክብሬ ፡ ነህና

አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ
አይሆንልኝም ፡ እኔስ
ያላንተ ፡ መኖር (፪x)

ዓይኔን ፡ በእጄ ፡ አልወጋም ፡ የጠራኝን ፡ ትቼ
እንዴት ፡ ነው ፡ ምኖረው ፡ ከአንተ ፡ ተለይቼ
ሌላው ፡ ሚመካበት ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ነገር
ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም

አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ
አይሆንልኝም ፡ እኔስ
ያለአንተ ፡ መኖር

ሲከብደኝ ፡ ብቸኝነቴ ፡ ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ በቤቲት
ቅዱሱን ፡ መንፈስ ፡ አልኩኝ ፡ እባክህ ፡ አትሂድብኝ

የሰው ፡ ጥማቱ ፡ ሌላ ፡ ነው
የኤኔ ፡ ግን ፡ አንድ ፡ ብቻ ፡ ነው
ያላንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም
ለአፍታ ፡ እንኳን ፡ አትተወኝ

ስለማልችል ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር
አትሂድብኝ ፡ ባክህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
እኔስ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ አልችልምና
ችላ ፡ አትበለኝ ፡ ክብሬን ፡ ክብሬ ፡ ነህና

ሳኦል ፡ ምን ፡ ነክቶት ፡ ከሰረ
ለሥጋው ፡ ምቾት ፡ ስለአደረ
አጥፋልኝ ፡ ብለህ ፡ ስትልከው
ያማረውን ፡ ለኤራሱ ፡ አስቀረው

በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ተታሎ
በድፍረት ፡ ሲጓዝ ፡ አይ ፡ ብሎ
ድምጽህን ፡ ንቆ ፡ ሲወጣ
መንፈስህ ፡ ሸሽቶ ፡ ተቀጣ

አጥፋልኝ ፡ ያልከውን ፡ አጠፋዋለሁኝ
ሰዋልኝ ፡ ያልከውን ፡ እሰዋዋለሁኝ
ዝክሩን ፡ ከምድር ፡ ላይ
መንግሥቱን ፡ አፍርሼ
አስደስትሃለሁኝ ፡ ቃልህን ፡ ጠብቄ

አዝ፦ አልችልበትም ፡ እኔስ
አይሆንልኝም ፡ እኔስ
ያላንተ ፡ መኖር (፪x)