ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ (Wede Mekdesu Segeba) - እንድርያስ ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንድርያስ ፡ ሃዋዝ
(Endrias Hawaz)

Lyrics.jpg


(Volume)

ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
(Wede Mekdesu Segeba)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንድርያስ ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endrias Hawaz)

ወደ መቅደሱ ስገባ
   ድምጼን ላሰማ በምስጋና
   በፍቅሩ ስቦ የመከረኝን
   ባማረ ስፍራ ያስቀመጠኝን
   ከፍ ላድርገዉ እግዚአብሄርን

አንድ ጊዜ አይደለም ሁለት ጊዜ
ጌታ የመከረኝ በግሳጼ
እንደ እኔማ ቢሆን እንደ ሀጢያቴ
የቁጣ ልጅ ነበርኩ ከፍጥረቴ
ዛሬ ግን መክሮኝ ሰዉ ሆኛለሁ
በመቅደሱ ዉስጥ አዜማለሁ

አሁን ዞር ብዬ ከኅላ ሳየዉ
መራራዉ ህይወቴ ዛሬ የጣፈጠዉ
እንዴት ያለዉን ሰዉን ለወጥከዉ
አምላኬ እግዚአብሄር ስራህ ድንቅ ነዉ
ገመድ ባማረ ስፍራ ወድቃልኝ
ባምላኬ ርስቴ ተዋበችልኝ

አንካሳ ነበረኩ መሄድ የማልችል
እውርም ነበርኩ ማየት የማልችል
የሱስ የሚባል አንድ ወዳጅ አይቶኝ
በእጆቹ ዳሶኝ በድንቅ ፈወሰኝ
እንደርሱ ያለ የለኝምና
ዛሬም ቆሜያለሁ በምስጋና

ጌታ እግዚአብሔር እረ እኔ ማን ነኝ
ለዚህ የክብር ህይወት ያጨኸኝ
አይገባኝም ይህ ለኔ አይደለም
ከሰው ሁሉ የማንስ ሃጢያተኛ ነኝ
አንተ ካረግከው ምን እላለሁ
ይኸው ለክብርህ አዜማለሁ