ሕይወቴ ነው (Hiwote New) - እንድርያስ ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንድርያስ ፡ ሃዋዝ
(Endrias Hawaz)

Lyrics.jpg


(Volume)

ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
(Wede Mekdesu Segeba)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንድርያስ ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endrias Hawaz)

አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው
ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለኝ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለኝ

ኦ! ለእኔስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ለነፍሴ ፡ ሰጪ ፡ እርካታ ፡ አለኝ ፡ ለኔ ፡ ውድ ፡ ጌታ

አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው
ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለኝ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለኝ

ሰላሜ ፡ እንደ ፡ ወንዝ ፡ ጅረት ፡ የሚፈስ ፡ ነው ፡ ሳያቋርጥ
የሰላም ፡ ምንጩ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ደስታውም ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው

አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው
ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለኝ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለኝ

እረፍቴ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ በበጎቹ ፡ እረኛ ፡ ላይ ፡ ነው
እረፍቴን ፡ የሚያደፈርስ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ካለኝ ፡ ኢየሱስ

አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው
ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለኝ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለኝ