ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (Des des Yelegnal) - እንድርያስ ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንድርያስ ፡ ሃዋዝ
(Endrias Hawaz)

Lyrics.jpg


(Volume)

ወደ ፡ መቅደሱ ፡ ስገባ
(Wede Mekdesu Segeba)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንድርያስ ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endrias Hawaz)

አዝ፦ ደስ ደስ ይለኛል እግዚአብሄርን ስጠራ
ደስ ደስ ይለኛል ስለእየሱስ ሳወራ
በምስጋና ሆኜ ከልቤ ፍቅሩን ምህረቱን አስቤ (2x)

በጌታ ጥላ ውስጥ በክንፉ አድሬ
የሱን ድንቅ ስራ አውርቼ መስክሬ
ልጨርስ ልፈጽም አቅቶኛልና
እንዲያው በዝማሬ እላለሁ ምስጋና (2)

አዝ፦ ደስ ደስ ይለኛል እግዚአብሄርን ስጠራ
ደስ ደስ ይለኛል ስለእየሱስ ሳወራ
በምስጋና ሆኜ ከልቤ ፍቅሩን ምህረቱን አስቤ (2x)

ምንም አላደረኩ ምንም አልሰጠሁት
አምላኬ ነው ብዬ ዋጋን አልከፈልኩት
እንዲያው በፀጋው ሀይል ደግፎኛልና
ለዚህ ክቡር ጌታ ይድረሰው ምስጋና (2x)

አዝ፦ ደስ ደስ ይለኛል እግዚአብሄርን ስጠራ
ደስ ደስ ይለኛል ስለእየሱስ ሳወራ
በምስጋና ሆኜ ከልቤ ፍቅሩን ምህረቱን አስቤ (2x)

ተስፋ እየቆረጥኩ ስወድቅ ስነሳ
ሸለቆ ወርጄ ውለታውን ስረሳ
ጌታ ይባርከኛል በፀጋው እንደገና
ህያው አምላኬ ነው ልቅረብ በምስጋና (2x)

አዝ፦ ደስ ደስ ይለኛል እግዚአብሄርን ስጠራ
ደስ ደስ ይለኛል ስለእየሱስ ሳወራ
በምስጋና ሆኜ ከልቤ ፍቅሩን ምህረቱን አስቤ (2x)