ይነጋል (Yenegal) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(1)

ጸሐፊ (Writer): Jos
(Jos
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

ሁኔታዬን ሳላይ ሀሀ አመሰግናለሁ ሀሀ
ቢሆንም ባይሆንም ሀሀ እግዚአብሄር ትልቅ ነው ሀሀ
አመሰግናለሁ እባርከዋለሁ ምስጋናን ሚሰዋ
ያከብረዋልና ለርሱ ይሁንለት ክብርና ምስጋና
     ምድር ዞሮ ቢመሽ በኛ ላይ
     ጀንበር ጠልቆ ቢጨልም ሰማይ
     አራዊት አርፈው ጎሬ ቢገቡም
     ጠዋት ደስታ አለ መንጋቱ አይቀርም
  ይነጋል ይነጋል የንጋትም ተራው ጸሀይ ይሆናል ይወጣል
           እንደ ወራጅ ሀሀ ወንዝ እንደ ውሀ ጅረት ሀሀ
           እንደሚፈሰው ሀሀ በጋና ክረምት ሀሀ
           ክብርና ሙገሳ ሀሀ ለርሱ ይሁንለት ሀሀ
           ለውዴ ምስጋና ሀሀ አሁንም ይፍሰስለት ሀሀ
ይመስገን እግዚአብሄር ይመስገን ዛሬም ለዘላለም ስሙ ይግነን
ይገባዋልና የኔ ጌታ ምስጋና አምልኮ ክብር እልልታ
    ወቅትና ሁኔታ አይለውጠውም
    የኑሮ መስፈሪያ ከቶ አይወስነውም
    ከሁኔታ በላይ እግዚአብሄር ትልቅ ነው
    ቢሆንም ባይሆንም እርሱ ትክክል ነው
ይመስገን እግዚአብሄር ይመስገን ዛሬም ለዘላለም ስሙ ይግነን
ይገባዋልና የኔ ጌታ ምስጋና አምልኮ ክብር እልልታ
   ስለሆነው ስላልሆነው ነገር እግዚአብሔር ይክበር ስሙ ይክበር እርሱ ከፍ ከፍ ይበል
   ስሙ ይክበር ስሙ ይክበር ስሙ ይክበር