ይገርማል ፡ ፍቅሩ (Yegermal Feqru) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

1.ሸክም አንገላቶኝ ሲያይ መንከራተቴን
  ደርሶ ፈታታልኝ ትብታብ እስራቴን
  ዛሬ ታውጆልኝ ሙሉ አርነቴ
  በደስታ ኖራለሁ በርሱ በረድኤቴ
      ፍቅሩ ማርኮ የራሱ አረገኝ
      አስደናቂው ጸጋ ለወጠኝ
      ይገርማል ፍቅሩ ይገርማል
      ይገርማል ጸጋው ይገርማል
      
አደራረጉ ገረመኝ አሰራሩ አስደነቀኝ ያሳየኝ ፍቅር ገረመኝ መውደዱ አስደነቀኘ 2x
የጌታዬ የየሱሴ የመድህኔ 2x
       2.ጊዜ ጊዜን ተካ ሰአታት አለፉ
            ቀናት ተደመሩ ሳምንታት ከነፉ
          ቢለዋወጡ ወራትና አመታት
          ፍቅርህ አይለወጥ ለዘመን ዘመናት
           ማንነትህ የሱስ ይገርማል
          ከመታወቅ እጅጉን ያልፋል
          ይገርማል ፍቅሩ ይገርማል
          ይገርማል ጸጋው ይገርማል /2/
   
አደራረጉ ገረመኝ አሰራሩ አስደነቀኝ ያሳየኝ ፍቅር ገረመኝ መውደዱ አስደነቀኘ 2x የጌታዬ የየሱሴ የመድህኔ 2x

3.ላከበረኝ ጌታ ምኔን እሰጣለሁ
  ከጥፋት ላዳነኝ ምኔን እከፍላለሁ
  ዋጋ አይተምነው ቆጥሬ እንዳልከፍለው
  ጨምሬ ጨምሬ አመሰግናለሁ
             ይብዛለት ለርሱ ምስጋና
             ይጨመር ይገባዋልና 2x
  ሀ ሀ ሀሌሉያ
  ለ ለ ለዘላለም
    ጌታ የሱስ ክበርልኝ
    ላረከው ለዋልክልኝ
     አባብዬ ክበርልኝ
     ለዋልክልኝ