From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ትዝ ይለኛል ያን ጊዜ በክንድህ ስትደግፈኝ ያኔ
ስትረዳኝ ስታግዘኝ ስትቆም አብረኀኝ ከጎኔ
ከሁሉም በላይ ደግሞ ያደረክልኝ በጎልጎታ
ከጥፋትም ያዳንከኝ ሞተህልኝ በእኔ ፋንታ
ውለታህ ውለታህ ብዙ ብዙ ውለታ
ስጦታ ስጦታ እጅግ ብዙ ስጦታ
ውለታው ብዙ ነው ስጦታው ብዙ ነው
1.ሳስበው መውደድህን ያደረክልኝን
የሰራህልኝን የከፈልክልኝን ያንሁሉ እዳዬን
ውስጤ መች ዝም ይላል ተመስገን ይላል
ተባረክ ይላል ከፍ በል ይላል እልልም ይላል
ተባረክ ይላል ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል
ትዝ ይለኛል ያን ጊዜ ያን ጊዜ የልጅነቴ
ስትረዳኝ ስታግዘኝ ስትቆም አብረኀኝ ከጎኔ
አሁንም ማን አለኝ ያላንተ የለረድኤቴ
የምትረዳኝ አንተው ነህ አለቴ አምባ መድሀኒቴ
አለኝታ ስለሆንከኝ ጌታዬ ተመስገንልኝ
መከታ ስለሆንከኝ ጌታዬ ተባረክልኝ
ያን ጊዜ ረዳቴኅኝ
አሁንም አንተው ነህ ያለኅኝ
2. ባንዲያ ልጅህ በኩል ህይወትን ሰጥተኅኝ
ሰማያዊውን ርስት ወራሽ አረከኝ ልጅህ አረከኝ
የቱተብሎ የቱ ይተዋል ስንሩን አሻግረሃል
ብዙ ረድተኅኛል ከስጦታህ በላይ ራስህን ሰጥተሃል
የሰራኅው ውለታ ያሳየኅኝ ፍቅር ከመናገር ያልፋል
ውለታህ ውለታህ ብዙ ብዙ ውለታ
ስጦታ ስጦታ እጅግ ብዙ ስጦታ
ውለታው ብዙ ነው ስጦታው ብዙ ነው
|