ሌላውን ፡ የሚወድ (Lielawen Yemiwed) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

ሌላውን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2x
ወንድሙን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2x
ፍቅር ፍቅር ፍቅር (2x)
ፍቅርን ጎሎኛል ፍቅርን ስጠኝ እርቅን አስተምረኝ
    
     1.በሰውና በመላክት ቌንቌ ብናገርም እንኩዋን ፍቅር ግን ከሌለኝ
      እንደሚጮህ እንደናስ እንደጽናጽል ሆኚያለሁ ፍቅር ግን ከሌለኝ
      ቢኖረኝ የትንቢት ስጦታ ሚስጥርንም ብፈታታ ፍቅር ግን ከሌለኝ
      ተራሮችን ሚያፈራርስ ታላቅ እምነት ቢኖረኝም ያለ ፍቅር ከንቱ ነኝ
           ፍቅር አለኝ ብልም ተግባር ካላወቀው
           የመውደድ ፊደሌ አካል ከጎደለው
           ለራስ በራስ ሆኖ ሌላውን ካልዳሰሰ
           ሞልቶ ካልፈሰሰ ለወንድሙ ምኑን ፍቅር ሆነ

                          ሌላውን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2
             ወንድሙን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2x
ፍቅር ፍቅር ፍቅር (2x)
ፍቅር ጎሎኛል ፍቅርን ስጠኝ እርቅን አስተምረኝ

2.እጅና እግር ያውጣ ይስራ ይንቀሳቀስ ፍቅር ቃል ብቻ አይሁንብኝ
  ካለህ ለሌለው ስጥ እንደሚል ደስ ብሌኝ እንድለግስ ቸርነትን አስተምረኝ
  ሌላ ሌላውን የምልበት ከኔነት ያለፈ ፍቅር ይታይ በእኔ ህይወት
  በቃልህም እንዳዘዝከው ባለንጀራዬን እንደራሴ በንጹህ ልብ ምወድበት
    የተራበን እንዳበላ የተጠማን እንዳጠጣ የታረዘን እንዳለብስ የታመመን
    እንድጠይቅ የታሰረን እነዳይ እንዳስታውስ ኀላ እንዳልጠየቅ በጌታ ቀን

ሌላውን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2x
ወንድሙን የሚወድ የፍቅር ህይወት ስጠኝ2x
ፍቅር ፍቅር ፍቅር (2x)
ፍቅርን ፍቅርን ስጠኝ እርቅን አስተምረኝ