ከሆነው ፡ ሁሉ (Kehonew Hulu) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

ከሆነው በጎነት ከኔ ነው ምለው ምን አለ
ከሆነው መልካምነት ከራሴ ምለው ምን አለ
ያማረብኝ ባንተ ነው ሰው የሆንኩት ባንተ ነው
መዳኔ ባንተ ነው በጎልጎታው ስራህ ነው

1. የበገና ቃና የዝማሪዬ ሚስጥር
     መቆሜ ባንተ ነው ማገልገሌ በቤትህ
     ልጅህም መባሌ በራሴ አይደለም
     በጸጋህ ነው እንጂ ከኔ ነው ምለው የለም
       ከአለም ርኩሰት ከእሳት ያመለጥኩት ባንተ ነው
       ዛሬ ላይ መቆሜ ምህረትህ በዝቶ ነው ባንተ ነው
ከሆነው ሁሉ ከኔ ነው ምለው የለም/2/
ያማረብኝ ባንተ ነው ሰው የሆንኩት ባንተ ነው
መዳኔ ባንተ ነው መትረፌ ባንተ ነው

2. ያለፈውን ሁሉ ቆም ብዬ ሳየው
   የትዝታን መዝገብ የኋሊት ስገልጠው
    እንደማንነቴ የት ነበርኩ ይሄኔ
    ግን ማይገባኝ ተገብቶኝ ቤትህ አለው ዛሬ
    እዳዬን በሻርከው ሞቴን በወሰድከው ባንተ ነው
    ድቅድቅ ጨለማዬን ገፈህ ባበራኀው ባንተ ነው
    
ይቅርታህ ብዙ ነው ምህረትህ ሰፊ ነው ሰፊ ነው
     
ስለበዛው ስጦታህ ስለበዛው ውለታህ አመሰግንሀለው
ሁሉ ባንተ ካንተ ሁሉ ለአንተ ነው ላንተ ነው
ክብር ክብር ክብር ክብር ላንተ ይሁን ላንተ ይሁን ለዘላለም