ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (Gieta New Eyesus) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

ከስሞች የበላይ ታላቅ ስም ያለው
 የሰላም አለቃ ኢየሱስ ጌታ ነው
 ድንቅ መካር ሀያል አምላክ የተባለው
 የዘላለም አባት ጌታዬ ልዩ ነው
   ይለያል ኢየሱስ /2/ ጌታ ነው ኢየሱስ /2/
 1.በክብር በሞገስ ለሆነው ገናና
  አምልኮ ውዳሴ ይብዛለት ምስጋና
  ለሀያላን ሀያል ለሌለው አምሳያ
   ይብዛለት እልልታ አሜን ሀሌሉያ (4) ሀሌ ሀሌሉያ አሜን ሀሌሉያ
      ይብዛለት ምስጋና ይደርደር በገና
      ይደመር ዝማሬ ይጨመር ውዳሴ /2/
          ይብዛለት ይብዛለት ምስጋናዬ ይብዛለት /2/ ለየሱሴ ለአባቴ ይጨመር ይጨመር
                                     
2.ከድንግል ተጸንሶ ስጋን የለበሰው
  በድንቅ በተአምራት ሀይሉን የገለጠው
   ያስጨናቂውን ቀንበር ፈጽሞ የሰበረው
   ሲአልን ድል ነስቶ ባባቱ ቀኝ ያለው የሱስ ለየት ይላል፣ ምስጋና ይገባዋል
       ይብዛለት ምስጋና ይደርደር በገና
       ይደመር ዝማሬ ይጨመር ውዳሴ
           ይብዛለት ይብዛለት ምስጋናዬ ይብዛለት ለየሱሴ ለአባቴ ይጨመር ይጨመር /2)