ኢየሱስ ፡ ሰላሜ (Eyesus Selamie) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

ኢየሱስ ሰላሜ ኢየሱስ እረፍቴ
ኢየሱስ ደስታዬ እርሱ ነው ጉልቤቴ
ኢየሱስ ሰላሜ ኢየሱስ እረፍቴ
ኢየሱስ ደስታዬ እርሱ ነው ኣቅሜ

ኣምላኬ እጅግ ትልቅ ነው በነገሮች ኣይገመት
ሁኔታ ኣይቀያይረውም የእርሱን መልካምነት
  መልካም ነው መልካም ነው
  መልካም ነው መልካም ነው

ግዙፉ ተራራ ተናደ በየሱስ ተገፈፈ ያ ጨለማዬ
ቅርፊቱ ተነስቶ ብርሃን ወጣ ማየት ቻለ የታወረው ኣይኔ
ስራዬን ሰርተህ እኔን ስለቀየርክ ኣመሰግናለሁ
መራራ ህይወቴን ጣፋጭ ስላረከው እኔ ኣከብርሃለሁ
በሰው ኣይን ያልገባው ቦታም ያልተሰጠኝ የተዘነጋሁ ሰው ነበርኩኝ
እኔ ማን ነኝ ታዲያ ልትመርጠኝ ልትቀባኝ ለዚህ ክብር ልታበቃኝ
ከተጣልኩበት ኣነሳኀኝ እባርክሃለሁ
ረድኤቴን ውዴን ባለውለታዬን ኣመሰግናለሁ(እባርክሃለሁ)

ኢየሱስ ሰላሜ ኢየሱስ እረፍቴ
ኢየሱስ ደስታዬ እርሱ ነው ጉልቤቴ
ኢየሱስ ሰላሜ ኢየሱስ እረፍቴ
ኢየሱስ ደስታዬ እርሱ ነው ኣቅሜ

ኣምላኬ እጅግ ትልቅ ነው በነገሮች ኣይገመት
ሁኔታ ኣይቀያይረውም የእርሱን መልካምነት
  መልካም ነው መልካም ነው
  መልካም ነው መልካም ነው