From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
የሰው ልጅ መግባቢያ የቌንቌው ብዛቱ
በየጎሳው ያለው የባህል ይዘቱ
የሰውነት ተፈጥሮ ሞገሱ ውበቱ
የአፍንጫ ማሽተት የጆሮ መስማቱ
የበረዶ መንጣት የጸሃይ ድምቀቱ
የከዋክብት ብዛት የሰማይ ርቀቱ
የአበቦች መዋብ የመብል ማርካቱ
አቤት የአምላክ ስራ ግሩም ነው ፍጥረቱ
እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማን አለ
እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማንም የለም
እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማን አለ
እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማንም የለም
በሰማይ በምድር የለም አልነበረም ደግሞም አይኖርም
አአለወይ አአለወይ የየየለም የየየለም
ማንም የለም እንደግዚአብሄር ያለ/2/
2.ነገስታትም መጡ በታላላቅ ግርማ ነግሰውም አለፉ ሁሉም በየተራ
ሃያላንም ጠፉ ጀግኖችም አረጁ ሁሉም እንደ ጥላ ታይተው ተሰወሩ
በአለም ላይ ያለው ትንሹም ትልቁም አለመኖሩ ማርጀቱ ማለፉ አይቀርም
በጊዜ አይወሰን ዘላለማዊ ነው እኔ እኔ ነኝ እንዳለ ሁሌም እርሱ ያው ነው
እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማን አለ
እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማንም የለም
እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማን አለ
እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማንም የለም
በሰማይ በምድር የለም አልነበረም ደግሞም አይኖርም
አአለወይ አአለወይ የየየለም የየየለም
ማንም የለም እንደግዚአብሄር ያለ/2/
|