እግዚአብሔር ፡ ታማኝ (Egziabhier Tamagn) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

1.ያለውን ሊፈጽም እግዚአብሄር ታማኝ ነው
  ሰማይ እንኩዋን ሰምቶት ጸና ሁን እንዳለው
  እኔ ልመን እንጂ ልስማው ልታዘዘው
  በእምነት የቀዳሁት ውሀ ወይን ሆኖ አየዋለሁ
    ነገር ከብዶት አያውቅ ከቃሉ ምን ሊያመልጥ
    ሁሉ ተገዢ ነው እርሱን የሚያዳምጥ
    ማን ይቁዋቁዋመዋል ያለውን ያደርጋል
    እርሱ ይበል እንጂ በጊዜው ይሆናል
       ይሁን ብሎ ሰማይን ባለበት አኖረ
       ይሁን ብሎ ምድርን እንዲሁ ፈጠረ
       እሱ ካለ ካለ ይሆናል አከተመ
       እንዴት የሚለው ቃል ይተካል በሆነ

በቃሉ የሚገኝ እግዚአብሄር ታማኝ በጊዜው የሚደርስ እግዚአብሄር ታማኝ
ጩሐት የሚሰማ እግዚአብሄር ታማኝ ሰምቶ የሚመልስ እግዚአብሄር ታማኝ
     እርሱ እግዚአብሄር ነው ግኡዝ ይሰማዋል
           እርሱ እግዚአብሄር ነው ህያው ይሰማዋል
            እንዳለው እንዲያው ሁሉ ይሆናል
            የሁሉ ፈጣሪ ምን ይሳነዋል
              እሱ ካለ ካለ ይሆናል አከተመ
       እንዴት የሚለው ቃል ይተካል በሆነ

         1.ጩኅ ከተባልኩማ ልጩህ በመዘዋወር
       ያለመሰላቸት ያለማንገራገር
       ባዩን በመታመን ደጁንም በመጥናት
       በራስ ጉልበት ሳይሆን በእምነት ጀግንነት
         ቀኑ ሲደርስማ የጩኀቴ ገደብ
                   ተራራዬ ይናዳል እንደኢያሪኮ ግንብ
                    ሰው አበቃ ብሎ ዘግቶት የከደነው ነገር
                    ያንሰራራል ነፍስ ይዘራል አምላኬ ሲናገር
በቃሉ የሚገኝ እግዚአብሄር ታማኝ በጊዜው የሚደርስ እግዚአብሄር ታማኝ
ጩሐት የሚሰማ እግዚአብሄር ታማኝ ሰምቶ የሚመልስ እግዚአብሄር ታማኝ