From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ቤተመንግስት ሳለ በረት ተወለድህ
የነገስታት ንጉስ የባሪያን መልክ ያዝህ
ባበጀሕው መዳፍ ስቃይ መቀበልህ
ፈራጅነትን ትተህ ፍርዴን ተሸክመህ ሸንጎ ፊት መቅረብህ
ራስህን ለማዳን አለመሟገትህ
ሁሉን ማድረግ ስትችል እንደማትችል መሆንህ
ለኔ አይደለም ወይ በጦር መወጋትህ
ድልድይ ልትሰራልኝ ደምህን አፈሰስህ
በመስቀል የምተከው ለኔ ነው ይህን ተረድችያለሁ
የፈሰሰው ደምህ ማርኮኛል ከምት
ወደር የሌለው ፍቅርህ ማርኮኛል ከጨለማው መንደር
የሚያስደንቅ ብርሃን ወጣልኝ በየሱስ ይመስገን እግዚአብሄር(አባ ስሙ ይክበር)
የሱስ የሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ለዘላለም ስምህ ይክበር
አምልኮ ይገባሀል አንተ በሰማይ በምድር
ተመስተን ተመስተን ልበል እኔ ምስጋናን ልዘምር
ብዙ አለኝ የማወራው የተሰራልኝ ታምር
2.ነውሯን ባደባባይ በገሀድ አውጥተው
ገበናዋን ገልጠው እጅግ አሸማቀው
ለውግረት ዳኝነት ፈርደው እንድትፈርድባት
ኢያጎሳቆሏት ወዳንተ አመጧት በዲንጋይ ሊወግሯት
መች እንደፈራችው ዲንጋይ ዘነበባት
ዳግም አትስሪ ብለህ የምት ፍርድን ሽረህ በነጻ ለቀካት
ስለምህረትህ እኔም አለኝ ምለው
ከመሞት መዳኔ ጌታ ሆይ ባንተ ነው
በመስቀል የምተከው ለኔ ነው ይህን ተረድችያለሁ
የፈሰሰው ደምህ ማርኮኛል ከምት
ወደር የሌለው ፍቅርህ ማርኮኛል ከጨለማው መንደር
የሚያስደንቅ ብርሃን ወጣልኝ በየሱስ ይመስገን እግዚአብሄር(አባ ስሙ ይክበር)
የሱስ የሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ለዘላለም ስምህ ይክበር
አምልኮ ይገባሀል አንተ በሰማይ በምድር
ተመስተን ተመስተን ልበል እኔ ምስጋናን ልዘምር
ብዙ አለኝ የማወራው የተሰራልኝ ታምር
|