፩ ፡ መንገድ (1 Menged) - እንዳሻው ፡ ታሪኩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳሻው ፡ ታሪኩ
(Endashaw Tariku)

Endashaw Tariku 1.png


(1)

፩ ፡ መንገድ
(1 Menged)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳሻው ፡ ታሪኩ ፡ አልበሞች
(Albums by Endashaw Tariku)

መዳ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ን በየሱስ
       አዳ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ ኝ ኢየሱስ አሀሀሀሀ
1.ከምድር አፈር ያኔ የተበጁ
  በአምላክ አምሳል የተፈጠሩ
  እነዛ ጥንዶች መነሻ ናቸው
  ለምት ላበሳው በአለም ላለው
     ሀጥያትን አይተው ሐጥያትን ሰርተው
     በፍርድ አለንጋ ያኔ ተገርፈው
     መራራ መዘዝ ለልጆቻቸው
     አቀበሉዋአቸው ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ
ግን አንድ መንገድ አለ ወደ አብ መሔጃ
ግን አንድ መሲህ አለ ከጥፋት መዳኛ
አንድ መንገድ የሱስ ወደአብ መሄጃ
አንድ መንገድ የሱስ ከፍርድ ማምለጫ
      መዳን በየሱስ አዳኝ ኢየሱስ
      መዳን በየሱስ በርሱ ብቻ ነው መዳን ሚቻለው (2x)
2.ጠፍተን እያለን በጠላት መንደር
  ተጭኖን ሳለ የሀጥያት ቀንበር
   አምላክ ልጁን ላከልን እንዲፈልገን
   ቀንበራችንን አንዲሰብርልን
      እርሱም ወረደ ፈልጎ አገኘን
       ሸክማችንን ተሸከመልን
       ስራችንንም ሰርቶ ፈጸመልን
       ሸክም ላዛለን ማረፊያ ሆነን (ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ ኀ)
እውነትም መንገድም ህይወትም እርሱ ነው
ከአብ ሚያገናኘን ድልድይም እርሱ ነው
አንድ መንገድ የሱስ ወደአብ መሄጃ
አንድ መንገድ የሱስ ከፍርድ ማምለጫ
 መዳን በየሱስ አዳኝ ኢየሱስ
 መዳን በየሱስ በርሱ ብቻ ነው መዳን ሚቻለው (2x)

  3.ግን ዛሬም የየሱስን የምስራቹን ወንጌል
    ላልሰማችሁ ሁሉ ከምት እነደሚያድን
    ቃሉ እንደሚለው ነው ኢየሱስ ኣዳኝ ነው
     በመስቀል የዋለው ለአለም ሁሉ ነው
        ማንም በልቡ የሱስን ቢያምን
         አድነኝ ብሎ ጌታን ቢማጸን
         ስሙን ቢጠራው ያገኛል መዳን(ከፍርድ ያመልጣል)…
ግን አንድ መንገድ አለ ወደ አብ መሔጃ
ግን አንድ መሲህ አለ ከጥፋት መዳኛ
አንድ መንገድ የሱስ ወደአብ መሄጃ
አንድ መንገድ የሱስ ከፍርድ ማምለጫ
      መዳን በየሱስ አዳኝ ኢየሱስ
      መዳን በየሱስ በርሱ ብቻ ነው መዳን ሚቻለው (2x)