የማዕረግ ፡ መዝሙር (Yemaereg Mezmur) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

አዝ፦ የማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ
ያከበርከኝን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ተቀበለው
አምልኮዬን ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀበለው (፪x)

በህብህ ፡ ምሥጋናህ ፡ ውስጥ ፡ ትኖራለህና
በህዝብህ ፡ አምልኮ ፡ ውስጥ ፡ ትገኛለህና
እኔም ፡ አመሰግንሃለሁ
ሌላ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

አቤቱ ፡ በፈቃድህ ፡ ኃይልን ፡ ሰጥተኸኛል
በፊትህም ፡ ደስታ ፡ ደስ ፡ አሰኝተኸኛል
ክብሬ ፡ ዝምም ፡ እንዳትል ፡ ትዘምርልሃለች
ነፍሴም ፡ ያንተን ፡ ውለታ ፡ ለሁሉ ፡ ታወራለች

አዝ፦ የማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ
ያከበርከኝን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ተቀበለው
አምልኮዬን ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀበለው (፪x)

በህብህ ፡ ምሥጋናህ ፡ ውስጥ ፡ ትኖራለህና
በህዝብህ ፡ አምልኮ ፡ ውስጥ ፡ ትገኛለህና
እኔም ፡ አመሰግንሃለሁ
ሌላ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

በሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ፊት ፡ ለእኔ ፡ ያዘጋጀሃት
ለሚፈሩህም ፡ ደግሞ ፡ ሰውረህ ፡ ያስቀመጥካት
አቤቱ ፡ ቸርነትህ ፡ እጅግ ፡ በዝታልኛለች
የጽድቅንም ፡ ብድራት ፡ አዘጋጅታልኛለች

ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ
ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ (፪x)

የሌለህ ፡ ተወዳዳሪ ፡ ግርማህም ፡ እጅግ ፡ አስፈሪ
በሠማይና ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ የእኛስ ፡ እግዚአብሔር
መለወጥ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የለም
ያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ
ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ
ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ (፪x)

ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ
በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ እቀኝልሃለሁ
ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለሃልና
ላመስግንህ ፡ ዛሬ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና (፪x)

ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህም (፫x)
ለኃያልነትህ ፡ ፍጽማኤ ፡ የለህም (፫x)
ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህም (፫x)
ለኃያልነትህ ፡ ፍጽማኤ ፡ የለህም (፫x)
ገናና ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ገናና ፡ ነህ
ገናና ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ገናና ፡ ነህ (፬x)