ተስፋ ፡ አትቁረጥ (Tesfa Atequret) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

የምትሄድበት ፡ መንገድ ፡ ጨለማ ፡ ቢሆንብህም
በኃይለኛ ፡ ውሃ ፡ ውስጥ ፡ ሳትፈልግ ፡ ብታልፍም
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
መንገድ ፡ አዘጋጅቶ ፡ መውጫ ፡ ሚያበጅ ፡ ነው (ሃሌሉያ)

አዝ፦ ተስፋ ፡ ቆርጦ (ተስፋ ፡ ቆርጦ)
ለሚያዘግም (ለሚያዘግም) ፡ ለሚሄደው ፡ በጨለማ
አምላክ ፡ አለ (አምላክ ፡ አለ)
መሪ ፡ አለ (መሪ ፡ አለ)፡ ጩኸትህን ፡ ሁሉ ፡ የሚሰማ
ተስፋ ፡ አትቁረጥ (ተስፋ ፡ አትቁረጥ)
ወንድሜ ፡ ሆይ (ወንድሜ ፡ ሆይ) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወድሃል
ወደ ፡ እቅፉ ፡ (ወደ ፡ እቅፉ)
ጉያ ፡ ግባ ፡ (ጉያ ፡ ግባ) ፡ ኧረፍቱ ፡ ይመራሃል

ተራራው ፡ ከፊት ፡ ሆኖ ፡ የሩቁን ፡ ቢጋርድብሽ
ተስፋሽ ፡ ሁሉ ፡ ጨልሞ ፡ የተተውሽ ፡ ሲመስልሽ
ታምነሽ ፡ ጸንተሽ ፡ ቁሚ (ጸንተሽ ፡ ቁሚ)
በሰራዊት ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ በሚያሸንፍ (በሚያሸንፍ)
ሁሉን ፡ በሚረታ (ሃሌሉያ)

አዝ፦ ተስፋ ፡ ቆርጦ (ተስፋ ፡ ቆርጦ)
ለሚያዘግም (ለሚያዘግም) ፡ ለሚሄደው ፡ በጨለማ
አምላክ ፡ አለ (አምላክ ፡ አለ)
መሪ ፡ አለ (መሪ ፡ አለ) ፡ ጩኸትሽህን ፡ ሁሉ ፡ የሚሰማ
ተስፋ ፡ አትቁረጥ(ተስፋ ፡ አትቁረጥ)
ወንድሜ ፡ ሆይ (እህቴ ፡ ሆይ) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወድሻል
ወደ ፡ እቅፉ ፡ (ወደ ፡ እቅፉ)
ጉያ ፡ ግባ ፡ (ጉያ ፡ ግባ) ፡ ኧረፍቱ ፡ ይመራሻል

እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በፍቅሩ ፡ እውነተኛ
ለመንጋው ፡ የሚራራ ፡ ታማኝ ፡ የሆነ ፡ ኧረኛ
ከልብ ፡ ለሚጠሩት ፡ ፈጥኖ ፡ የሚደርስ
ለጥያቄ ፡ ሁሉ ፡ መልስ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (ሃሌሉያ)