ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም (Mesganawen Alresawem) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

ሃሌሉያ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ ነው !
ኦ ፡ ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ፡ ያደረገልንን ፡ እያሰብን
አንድ ፡ ላይ ፡ ጌታን ፡ እናመልከዋለን ።

አዝ፦ ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ
አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ (፪x)

ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ (፪x)

ምህረቱ ፡ እየበዛ ፡ ቁጣው ፡ ደግሞ ፡ እየዘገየ
ከሰው ፡ ልጆች ፡ሁሉ: ይልቅ: በምክሩ ፡ የተለየ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፬x)

አዝ፦ ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ
አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ (፪x)

ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ (፪x)

ህጉ ፡ ለእግሬ ፡ ብርሃን ፡ ሆኖ
ኢኸው ፡ ነፍሴን ፡ መልሷታል
በጽድቅ ፡ መንገድ ፡ እየመራ
በረከቱን ፡ አጥግቧታል
ክበር ፡ ብለው ፡ ያንስበታል
ንገሥ ፡ ብለው ፡ ያንስበታል
(፪x)

አዝ፦ (ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም) ፡ ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም) ፡ ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም
(ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ) ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ
(አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ) ፡ አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ (፪x)

ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ

(ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ) ፡ ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
(አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ) ፡ አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
(ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ) ፡ ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
(ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ) ፡ ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ

በመጥራቱ ፡ ሳይጸጸት
ወደመንግሥቱ ፡ አፍልሶኛል
አይጥለኝም ፡ አይተወኝም
በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል
ክብሬን ፡ ጥዬ ፡ ባመሰግነው
አይበዛበት ፡ ይህም ፡ ሲያንሰው ፡ ነው
(፪x)

አዝ፦ (ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም) ፡ ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም) ፡ ምህረቱን ፡ አልዘነጋውም
(ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ) ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በማዳኑ
(አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ) ፡ አመልከዋለሁኝ ፡ በየቀኑ (፪x)

ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ

(ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ) ፡ ያደረገልኝን ፡ ቆጥሬ
(አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ) ፡ አልጨርሰውም ፡ ተናግሬ
(ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ) ፡ ብዙ ፡ ነውና ፡ ምህረቱ
(ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ) ፡ ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ በየዕለቱ