ምሥጋናህ ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (Mesganah Zeweter Beafie New) - እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 2.jpeg


(2)

ምሥጋናውን ፡ አልረሳውም
(Mesganawen Alresawem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፬ (2001)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ አልበሞች
(Albums by Endalkachew Hawaz)

አዝ፦ ምሥጋናህ ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፬x)
ላመሰግንህ ፡ እወዳለሁ (፫x)
ላመሰግንህ ፡ እፈቅዳለሁ (፫x)

ቀንበረን ፡ ከጫንቃዬ ፡ ላይ ፡ ሰበርከው ፡ አሃሃሃ
የከበደኝን ፡ ሸክሜን ፡ አራገፍከው
ባዶነቴን ፡ በፍቅርህ ፡ ሞላኸው
ደስታዬን ፡ ከወይን ፡ ፍሬ ፡ ይልቅ ፡ አበዛኸው

ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ
ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ
እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x)

ምሥጋናህ ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፬x)
ላመሰግንህ ፡ እወዳለሁ (፫x)
ላመሰግንህ ፡ እፈቅዳለሁ (፫x)

በሕይወት ፡ መዝገብህ ፡ ላይ ፡ ስሜን ፡ ጻፍከው
ኑሮዬን ፡ ታሪኬን ፡ በሙሉ ፡ ለወጥከው
በደስታ ፡ ዘይት ፡ ራሴን ፡ ስትቀባ
ሰላምን ፡ ኢኸው ፡ በቤቴ ፡ ውስጥ ፡ ገባ

ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ
ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ
እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x)

ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x)
ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x)

ሊቋቋሙን ፡ ከቶ ፡ አልቻሉም ፡ ጠላቶቼ
በስምህ ፡ አሸነፍኳቸው ፡ ተዋግቼ
እግሬን ፡ በአንገታቸው ፡ ላይ ፡ አኑሬያለሁ
በደስታ ፡ የድል ፡ ዝማሬን ፡ ዘምራለሁ

መክበቡን ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኝ ፡ ነበረ
ያሰብክልኝ ፡ ስፍራ ፡ እንዳልደርስ ፡ ብዙ ፡ ጣረ
አንተ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ጥሰህ ፡ አሳለፍከኝ
ጠላቴ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ከፍ ፡ አረከኝ

ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ
ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ
እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x)

ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x)
ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x)